፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆቢርን የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ።
ጠቅላላ ጉባኤው ዶክተር አይናለም አባይነህን ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ሌሎች 9 የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን መርጧል።
ጉባኤው ላለፉት 6 ዓመታት የመሩትን የቦርድ አባላት ሲያሠናብት አዳዲሶቹን ክልሎች የምክር ቤት አባልነት ጥያቄ አጽድቋል።በዚህም መሠረት የደቡብ ክልል፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም የሲዳማ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ነው በአባልነት ያካተተው።
ጠቅላላ ጉባኤው ከቀረቡለት 3 የፕሬዝደንት፣ 4 የምክትል ፕሬዝዳንት እና 16 የቦርድ አባላት እጩዎች መካከል ነው የቦርድ አመራሮቹን የመረጠው።በሌላ በኩል ጠላላ ጉባኤው የቀረቡለትን የደንብ ማሻሻያዎች ተመልክቶ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ የሀገሪቱን የግሉ ዘርፍ ድምጽ እንዲያገኝ እና ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ለማድረግ አዲሱ አመራር የላቀ ኃላፊነት እንዳለበት እና እንዲወጣ ያሳሰቡት ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት መልአኩ እዘዘው (ኢንጅነር) በቆይታችውም የቻሉትን ሁሉ ስለማበርከታቸው ገልጸዋል።
በ2012 ዓም መካሄድ የነበረበት ጠቅላላ ጉባኤ በሰሜኑ ጦርነት፣ በኮቪድ ወረርሽኝ እና በሌሎችም ምክንያቶች ሲራዘም ቆይቶ ሐምሌ 11/2016 ዓም በአፍሪካ ኀብረት አዳራሽ በተሳካ መልኩ ተካሂዷል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











