፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-በጦርነት አስከፊ እሳት የሚለበለበው የጋዛ ሰርጥ ሌላ እና አዲስ ስጋት እንደተጋረጠበት ተሰምቷል።
በጋዛ ሰርጥ አስከፊው ጦርነት መቋጫ ባጣበት በዚህ ወቅት በዚያ ስፍራ ለህፃናት አስከፊ የፖሊዮ ወረርሽኝ ስጋት ተደቅኗል ነው የተባለው።የጋዛ ሰርጥ የጤና ባለስልጣናት በሰጡት ማብራሪያ የፖሊዮ አምጪ ቫይረስ መገኘቱን በይፋ አስታውቀዋል።
እንደ የጤና ባለስልጣናቱ ዝርዝር ማብራሪያ ቫይረሱ የተገኘው ብዙ ሺ ህዝብ ተሰባስቦ በሰፈረባቸው የስደተኞች እና ተፈናቃዮች መጠለያ ስፍራዎች ነው።

አሁን በተከሰተው የፖሊዮ ቫይረስ የተነሳም በሰርጡ ሌላ አሳዛኝ የጤና ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ነው የተገለፀው።
የፖሊዮ ቫይረስ በዋናነት የሚያጠቃው ህፃናትን ሲሆን የመተላለፊያ መንገዱ ደግሞ በንፅህና ጉድለት በተበከለ ውሃና ምግብ እንደሆነ ይታመናል ።ዘገባው የስካይ ኒውስ ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












