፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-በየመን አንሳር አላህ ወይም የሀውቲ ዓማፂያን በመባል የሚታወቁት ሀይሎች የቴላቪቭን ከተማ በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ማጥቃታቸውን አስታውቀዋል።
ኒውስዊክ ከሀውቲዎች አገኘሁት ባለው መረጃ የእስራኤሏ አንዷ እና ትልቋ ከተማ ከባድ ጥቃት አስተናግዳለች ነው ያለው ዛሬ ማለዳ ላይ የማዕከላዊ ቴላቪቭ ከተማ በከባድ ፍንዳታ ተናውጣለችም ነው ያለው ዘገባው ።
የእስራኤል የመከላከያ ሀይል በሰጠው ማብራሪያም ስለደረሰው ጥቃት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ነው የገለፀው።ዘገባው የሚያሚ ሄራልድ ነው
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











