፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 11 2016| NBC ETHIOPIA-የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው ከሰላሳ አምስት የአውሮፓ ሀገራት ለሚመጡ በቤላሩስ ቆይታ ለሚያደርጉና ለመውጣትም ለሚፈልጉ ሁሉ የጊዜያዊ ከቪዛ ነፃ ፍቃድ መስጠቷን አስታውቀዋል፡፡

ሉካሼንኮ በንግግራቸው የሀገራችንን ግልፅ አሰራርና ሰላማዊነት ለማሳየት እንዲሁም የመልካም ጉርብትና ምስክር የሆነውን ለየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ዜጋ በተለይም ከሰላሣ አምስት ሀገራት ለሚገቡ ከነገ የአውሮፓውያኑ ሀምሌ 19/2024 ጀምሮ ለሰላሳ ቀናት የሚቆይ ከቪዛ ነፃ ፍቃድ መስጠቷን እንገልፃለን ነው ያሉት፡፡ ዘገባው የአዘር ኒውስ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












