፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 11 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በአዲስ አበባ የኮድ 2 ተሸከርካሪ የፈረቃ እንቅስቃሴ ወደፊት በጥናት የሚሆን እንጂ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን እንደማይሆን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ‹‹ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው›› በሚል ርእስ በተቋሙ ባለሙያ ለሚዲያ የተሰጠው ማብራሪያ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አቋም አለመሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
ግለሰቡ ‹‹ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል›› ያሉት ከተቋሙ ያገኙትን መረጃ ተንተርሰው አለመሆኑ ተገልጿል፡፡
ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ ወደ ፊት ከመንግስት በሚሰጥ አቅጣጫ ተጠንቶ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ እንደሌለ ተቋሙ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












