፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 11 2016| NBC ETHIOPIA-“የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ6ተኛ ዙር በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የኩባንያው ጽህፈት ቤቶች የችግኝ ተከላ አካሂዷል።
የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከሀምሌ 11 እስከ 30 በተቋሙ የሚካሄድ ሲሆን 500ሺ ችግኞች እንደሚተከሉ ተገልጿል ።
ተቋሙ ላለፉት አምስት አመት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመላው ሀገሪቱ 3.8ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍረህይወት ታምሩ ገልጸዋል ።በዚህም 20ሺ ለሚሆኑ ዜጎች በጊዚያዊነት የስራ እድል መፍጠሩ ስራ አስፈጻሚዋ አክለው ተናግረዋል።
በ -ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












