፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 06 2016| NBC ETHIOPIA- የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) በ2017 ዓ.ም የክልሉ መንግሥት ረቂቅ በጀት ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ካቢኔው በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቀረበለትን የ2017 የበጀት አመት ረቂቅ በጀት መርምሮ በማፅደቅ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል። በዚህም መሰረት በክልል ደረጃ ከተያዘው በጀት 56 በመቶ ለካፒታል በጀት የተመደበ ሲሆን 42 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው ተብሏል።

የበጀቱ ምንጭም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች የሚሰበሰብ ገቢ እንዲሁም ከፌዴራል መንግሥት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀመር ለክልሎች የሚሰጥ ድጎማና ከሌሎች ምንጮች ታሳቢ መደረጉ ተገልጿል። በጀቱ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀርም የ22 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ነው የተገለፀው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












