፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአርባ ምንጭ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባኤው ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያቀርቡ ሲሆን ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽም ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የ6ኛ ዙር 3ኛ አመት የ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን፣ የክልሉ ምክር ቤት የ2016 በጀት አመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን እና የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በቆይታው የክልሉ የ2017 በጀት ረቂቅ የበጀት አዋጅን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












