፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA- ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ ያነጣጠረ የጨረር ጦር መሳሪያ በህዋ ላይ ልታሰማራ መሆኑ ተገለጸ ፡፡
ደቡብ ኮሪያ በዚህ ዓመት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመምታት የጦር መሳሪያ እንደምታሰማራ የሀገሪቱ ወታደራዊ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ደቡብ ኮሪያ ይህንን ፕሮግራሟን Star Wars ፕሮጀክት ስትል ጠርታዋለች፡፡
ድሮን-ዛፒንግ የጨረር ጦር መሳሪያ በደቡብ ኮሪያ ጦር በሀንውሀ ኤሮስፔስ የተሰራ ፤ ውጤታማ እና ርካሽ ዋጋ ያለው ሲሆን በስውር ወታደራዊ መረጃዎችን በመስጠት አገልግሎቱ ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ኮርያ የመከላከያ ፕሮግራም አስተዳደር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ሀገራችን የጨረር ጦር መሳሪያ በማሰማራት እና በመተግበር ከዓለም ቀዳሚ በመሆኗ በሰሜን ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ ለሚሰነዘረው ጥቃት የሰራዊታችን ምላሽ አቅም የበለጠ እንዲጠናከር እድል ይፈጥራል ሲሉ የደቡብ ኮርያ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የሲኦል ባለስልጣናት ስለ አዲሱ ፕሮጀክታቸው ይህንን ቢሉም ከፒዮንገያንግ በኩል ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ አንስቶ የተባለ ነገር የለም ፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












