፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA-በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ለብሪክስ አባል ሀገራት በተዘጋጀ ፓርላሜንታዊ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ ገብቷል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ በሰፈረው መልዕክት ጉባኤው በሩሲያ ሰይንት ፒተርስበርግ ከተማ የተዘጋጀ ሲሆን ሐምሌ 11 እና 12/2024 እ.ኤ.አ የሚካሄድ ነው፡
ጉባኤው በዛሬው ውሎው የብሪክስ/BRICS/ ሀገራት በተለያዩ የባለ ብዙ ወገን የግንኙነት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየመከረ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በዚህ ጉባኤ የአባል ሀገራቱን ትብብር እና ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ ፕሮቶኮል እና በጋራ መሥራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙም እንዲሁ፡፡
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ፓርላማ አቋም እና የግንኙነት ዝግጁነትን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር አማካኝነት ገለጻ መደረጉም ተገልጿል፡፡

መድረኩ በሁለት ቀን ውሎው በእነዚህና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክሮ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












