፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 03 2016| NBC ETHIOPIA-በአዲስ አበባ በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማዋን አረንጓዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ።
በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺህ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺህ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ ጉዳት በማድረሳቸው ከ150 እስከ 300 ሺህ” ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል።
ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀምና በመንከባከብ እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣትና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ የከተማ አሰተዳደሩ ማሳሰቡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












