፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 03 2016| NBC ETHIOPIA- የ2016 የትምህርት ዘመን አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀመሯል፡፡
ፈተናውን የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ተገኝተው አስጀምረውታል።
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኦን ላይንና በወረቀት ነው የተዘጋጀው።
በኦን ላይን ፈተናውን ለሚወሰዱ ተማሪዎች ሰፊ ጊዜ ተሰጥቷቸው ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ፈተናው በዛሬው ዕለት በመላው አገሪቱ በተመረጡ የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ ሰዓት መሰጠት ጀምሯል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












