፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 02 2016| NBC ETHIOPIA- የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ቅናሽ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ።
በዚህ መሰረትም የሰኔ ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 19 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች 22 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግም 15 ነጥብ 8 በመቶ በመሆን መመዝገባቸው ተገልጿል።
በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በግንቦት ወር ከነበረበት 23 ነጥብ 3 በመቶ ወደ 19 ነጥብ 9 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












