፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 29 2016| NBC ETHIOPIA- በፈረንጆቹ 2024 የዓለማችን ሀያል በሆነቸው አሜሪካ ቢጎበኙ ያላቸውን ምርጥ ከተሞች ሲ ኤን ኤን ትራቭል በድህረ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡ በሀገሪቷ ግዛቶች ከሚገኙ ከተማች መካከል ባላቸው መስህቦች፣ የምግብ እና የመጠጥ አቅርቦቶች እና ታሪካዊ ስፍራዎች በማካተት ነው የ10 ከተማዎችን ዝርዝር ይፋ ያደረገው፡፡ ከ50,000 እስከ 225ሺ ነዋሪዎች የሚገኙባቸው ከተሞች በሪፖርቱ መካተታቸውን ድህረገጹ አስፍሯል፡፡ ሲ ኤን ኤን በትራቭል ከዘረዘረቸው ከተሞች አምስቱን እናስቃኛችሁ፡፡
መገኛዋ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሳን ሉዊስ ኦቢስፖ ከተማ ድህረ ገጹ ቢጎበኙ ካላቸው የአሜሪካ ከተሞች በ5ተኛ ደረጃ አስቀምጧታል፡፡

በካሊፎርኒያ ማዕከላዊ የባህር ጠረፍ ላይ የሚትገኘው ከተማዋ ከዓመት በፊት በተደረገ የህዝብ ቆጠራ 50ሺ ነዋሪዎች ይገኙባታል፡፡ ሳን ሉዊስ ኦቢስፖ የተመሰረተው እ.ኤ.አ በ1772 ዓ.ም በስፔኑ ሴንት ጁኒፔሮ ሴራ ነው፡፡ ሳን ሉዊስ ኦቢስፖ በታሪካዊ አርክቴክቸር፣ በወይን እርሻዎች እና በእንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም በካሊፎርኒያ ፖሊቴክኒክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምትታወቅ ሲሆን የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ ከተማ ናት። ሳን ሉዊስ ኦቢስፖ የእረፍት ቀናት ለማሳለፍ ተወዳጅ ከተማ ስትሆን ለእግር ጉዞ፣ ለግብይት፣ የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦችን ለማግኘት ተመራጯም ናት፡፡
በሁለት መንገዶች መካከል የሚገኘው ገም ዎል የሚባለው ግርግዳ በከተማዋ መሀል የሚገኝ ሲሆን ሰዎች ማስቲካን በመጠቀም የተለያዩ ጽሁፎችን እና ስእሎችን የሚስሉበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ጠባብ ስፍራ ሁሌም በሰዎች የተጨናነቀ ነው፡፡ እጅግ ቅንጡ እና ታዋቂው ማዶና ኢን ቱሪስቶች በከተማው በሚኖራቸው ቆይታ ሳያርፉበት የማይሄዱት ሆቴል ነው፡፡ ጥንታዊ ይዘት ያለው ማዶና ኢን ባህላዊ ምግቦቹ እና መጠጦቹ ተወዳጅ ሲሆኑ የመዋኛ ገንዳ እና ሌሎች የቱሪስትን ፍላጎት የሚያሟሉ አገልግሎቶችን ይዟል፡፡እ.ኤ.አ. በ2022 የከተማው ቱሪዝም ቢሮ ባደረገው ዳሰሳ ፣ 7.47 ሚሊዮን ጎብኚዎች ከተማዋን ጎብኝተዋታል፡፡
በሜይን ግዛት በርካታ ህዝብ የሚኖርባት ከተማ እና የኩምበርላንድ ካንትሪ ዋና መቀመጫ ናት በሜን ግዛት የምትገኘው ፖርት ላንድ፡፡ እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2020 የፖርትላንድ ህዝብ ብዛት 68ሺ 408 ነበር።

የፖርትላንድ ወደብ እ.ኤ.አ በ2019 በኒው ኢንግላንድ ሁለተኛው ትልቅ የባህር ወደብ ሊባል ችሏል፡፡ ፖርትላንድ ስያሜዋን ያገኘችውም ከተማዋ በባህር የተከበበች በመሆኗ ነው፡፡ ይህም ቱሪስቶች ከተማዋን እንዲጎበኙ ሰፊ እድልን ፈጥሯል፡፡ ቀልብን በሚስቡ አበባዎች እና አረንጓዴ ስፍራዎች የተከበበችው ከተማዋ ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ኪነ ህንጻዎች በስፋት ይገኙባታል፡፡
ጣፋጭ ምግቦች እና መጠጦች በብዛት የሚገኙባት ፖርትላንድ ምቹ የትራንስፖርት አማራጮች፣ ጥንታዊ ስፍራዎች እና የመንገድ ዳር ገበያዎች የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2022፣ የፖርትላንድ ቱሪዝም 5.2 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ገቢ አግኝቷል፡፡ ሲ ኤን ኤን በትራቭል ድህረ ገጹ ቢጎበኙ ካላቸው ከተሞች በ4ተኛነት አስፍሯታል፡፡
እ.ኤ.አ በ 2022 221ሺ 776 ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች መዳረሻቸው ሲያደርጓት የከተማው ህዝብ 1 ሚሊዮን እንደሚሰርሱ ይገመታል፡፡ በአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽግተን የምትገኝ ሲሆን ቱሪስቶች ከተማዋን እንዲጎበኟት በ3ተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡ የታኮማ ከተማ

ከተማዋ የታዋቂው የመስታወት አርቲስት ዴል ቺሁሊ የትውልድ ቦታ ሲሆን በመስታወቶች ላይ የተሰሩ ተለያዩ ጥበቦችን የያዘ የመስታወት ሙዚየም አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዋሽንግተን ታሪክን ወደ ኋላ የሚያስመለክቱ ቅርሶችን የያዘ ሙዚየም በከተማዋ ይገኛል፡፡ የዱር እንስሳት ማቆያ፣ ጥንታዊ ተሸርካሪዎች እና ጀልባዎች የሚገኙበት ማዕከል፣የቢራ ፋብሪካ እንዲሁም ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ ቀላል ምግብ እና መጠጥ የሚያዘጋጁት ካፌዎች መገኛ ጭምር ናት፡፡በከተማዋ የሚከናወኑ የሙዚቃ ድግሶች በአብዣኛዎቹ ቱሪስቶች ተወዳጅ እና የተዝናኖት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉበት ስፍራ ናቸው፡፡
በወንዝ ዳር የሚደረገው የወተር ፋየር ወይም በእሳት የሚከናወን ጨዋታ ከተማዋ የምትታወቅበት ፌስቲቫል ነው፡፡ወተር ፕሌስ ፓርክ የተሰኘው ስፍራ ቱሪስቶች ሰላማዊ ጊዜን ለማሳለፍ የሚመርጡት ቦታ ሲሆን መገኛው በሮድ አይስላንድ ግዛት ፕሮቪደንስ ከተማ ነው፡፡ ሮገር ዊሊያምስ የተሰኘው እውቁ እና ጥንታዊው የዱር እንስሳት ማዕከል ሌላኛው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ ነው፡፡እ.ኤ.አ በ1895 ግንባታው ተጀምሮ በ1904 የተጠናቀቀው ሮድ ደሴት ግዛት ህንጻ ለግዛቲቱ የተወካዮች ምክር ቤት በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡ ፕሮቪደንስ ፐርፎርሚንግ አርት ሴንተር የብዙ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስብ ጥንታዊ ቦታ ነው፡፡ እ.አ.አ በ27.7 ሚሊዮን ቱሪስቶች ከተማዋን የጎበኙ ሲሆን ድህረገጹ ቢጎበኙ ካላቸው ከተሞች በ2ተኛ ደረጃን አግኝታለች፡፡
ሪችመንድ ከተማ በታሪክ፣ በሥነ ጥበብ እና በባህል ሀብቷ ታዋቂ ነች። የከተማዋ ሙዚየሞች የሀገሪቷን እና የቨርጂኒያ ግዛትን ቅርሶችን አካቶ በመያዟ በብዙ ቱሪስቶች ዘንድ ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል፡፡ በየዓመቱ ከ16 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተማዋን የሚጎበኙ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 229,395 የህዝብ ብዛት ነበራት፡፡ የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ሙዚየም ፣የሆሊውድ ሀውልት፣ሮያል ፓርኮች እና መናፈሻዎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ቲያትሮች፣ ጋለሪዎች እና ሙዚየሞች፣ ከተማዋ በጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ሲ ኤን ኤን ትራቭል በድህረ ገጹ ቢጎበኚ ካላቸው ከተሞች የቀዳሚውን ስፍራ ይዟለች፡፡












