፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 01 2016| NBC ETHIOPIA-በሐረሪ ክልል የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች 26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

በክልሉ ከተማና ገጠር ወረዳዎች የተገነቡትን የልማት ፕሮጀክቶችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ መርቀው ከፍተዋል።
ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የድሬጠያራ 2ኛ ደረጃ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ የአው በርኸድሌ ታሪካዊ መንደር እና የሱቅጣጥ በሪ እድሳት እና ጥገና ፕሮጀክት እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከያ ማዕከል ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።
የ26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በዓል እተየከበረ ከሚገኝባቸው ሁነቶች መካከል ዘላቂ ፋይዳ ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች ምረቃ አንዱ መርሃ ግብር ነው ተብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












