፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 29 2016| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዘንድሮውን ሁለተኛ ዙር የሁለተኛ ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ አስጀምረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፦ አዲስ አበባን አረንጓዴ በማልበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ውብ ከተማ ለማድረግ ሁላችንም ችግኝ መትከል አለብን ብለዋል።
የከተማዋ የአረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ 20 ሚሊየን ሀገር በቀል ዛፎች፣ ለምግብነት የሚውሉ እና ለውበት የሚሆኑ ችግኞችን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚተከሉ ገልጸዋል።
ባለፉት ጊዜያት ከተተከሉ ችግኞች 89 በመቶ የጽድቀት መጠን እንዳለው ገለጸው መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባክብ እንዲጸድቁና ፍሬ እንዲያፈሩ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለውም መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ አሻራውን ሊያኖሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ዠንጠራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መጎስ ባልቻን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ መምህራን፣ አትሌቶች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












