፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 20 2016| NBC ETHIOPIA-በመላው አለም ተፅዕኖ መፍጠር ከቻሉ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች መካከል ቀዳሚው ነው፤ በእያንዳንዱ ሳምንት የሚተላለፈውን የቀጥታ ስርጭት ከ10 ሚሊየን በላይ ተመልካቾች እንደሚመለከቱትም ይነገርለታል፤ የብዙዎችን ታሪክ የቀየረ እንዲሁም የመታየት እድልን የፈጠረ ፤ በርካቶች እውቅናን እንዲቸሩ በማድረግ የተደበቀን ጥበብ ፈልጎ በማውጣት ረገድ የሚስተካከለው እንደሌለም ብዙዎች ምስክር የሚሰጡለትም ነው-አሜሪካን ጎት ታለት
የአሜሪካውያኑ ታለንት ሾው ውድድር ወይንም ኤጂቲ በፈረንጆቹ 2006 ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያለው፡፡ የሀሳቡ ፈጣሪ ሳይመን ኮውል ከዚህ ቀደም በሀገረ እንግሊዝ ፕሮግራሙን ጀምሮት የነበረ ሲሆን እርሱን በመተው በ2006 ወደ አሜሪካ በመጓዝም ለአሜሪካው ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ሀሳቡን በመሸጥ ዳግም ወደ ቴሌቪዥን እንዲመጣ ሆኗል፡፡

የአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚሸልመው ውድድሩ በብዙ ሚሊዮኖች የሚታይ በመሆኑ ማንኛውን አይነት ታለንት እንዲወደድ አድርጎ በማቅረብ ሌሎች የዕድል በሮች እንዲከፈቱ በማስቻል ረገድ ተወዳዳሪ የለው ይባልለታል፡፡ ከአሜሪካ ባለፈ በመላው አለም የሚገኙ ሰዎች ወደ ስፍራው በማቅናት እድሉን ለማግኘትም ይጥራሉ፡፡
ታዲያ በብዙ ጥረት ተሳክቶላቸው ለአለም ታለንታቸውን ለማሳየት እና ለማስገረም የቻሉ እድለኞች በርካቶች ናቸው፡፡
ኤጂቲ ባለፉት 18 አመታት ቆይታው ታዲያ በመድረኩ ከደመቁ ፤ ዳኞችን እና ሌሎች ተመልካቾቸን እጅ በአፍ በማስጫን የጎልደን በዘር ካገኙ ተወዳዳሪዎች መካከል ጥቂቶቹን እናስቃኛችሁ፡፡
በ14ኛው የአሜሪካን ጋት ታለንት ምዕራፍ ላይ ብቅ በማለት ዝናን ካገኙ የድምፅ ተወዳዳዎች መካከል አንዱ ነው-ኮዲ ታሂዲን ሊ

ይህ የ22 አመት ወጣት ከልጅነቱ አንስቶ ማየት የማይችል ከመሆኑም በላይ የኦቲዝም ተጠቂ እንደሆነም ወላጅ እናቱ በአሜሪካን ጎት ታለንት መድረክ ላይ ትናገራለች፤በዚህ ወቅት ዳኞቹ በማዘን እና ምን አይነት ስራ ይዞ ሊቀርብ ነው ታዲያ በሚል ግራ የመጋባት 2 ስሜት ውስጥ በመሆን ለሚያቀርበው ስራ መልካም እድል እንዲሆንለት በመመኘት መድረኩን ይሠጡታል፡፡
የአካል ጉዳት ሆነ ሌላ ማንኛውም ችግር ከሚፈልጉት ለመድረስ እንደማይገድብ በመድረኩ ዳግም ሊያረጋግጥ ብቅ ያለው ኮዲ ፒያኖውን በጣቶቹ እየነካካ በሚያወጣው ድምጽ መላው አለምን አስደንቋል፡፡በስራው እጅግ ከተደመሙት ዳኞች መካከል ጋብርኤላ የተሰኘችው ዳኛም በቀጥታ ወደ ግመሽ ፍጻሜ እንዲያልፍ የሚረዳውን ጎልደን በዘር ሰጥታዋለች፡፡
ከአሜሪካን ጎት ታለንት ሌላው የምንግዜም አይረሴ የሆነው የጎልደን በዘር አሸናፊው ደግሞ ዳንቼስ ይሰኛል፤60ኛ አመቱ ላይ የሚገኘው ይህ ግለሰብ ዳኞችን ጨምሮ ከመድረክ ጀርባ የሚገኙትን ባለሞያዎች ጭምር ማንቀሳቀስ የቻለ ስራን በማቅረብ የምንግዜም አስቂኝ እና አይረሴ የጎልደን በዛር አሸናፊም ሆኗል፡፡
በታለንት ሾ ውድድር ላይ አይነተ ብዙ ስራዎችን ይዘው ወደ መድረክ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ብዙ ናቸው፤ ከነዛ መካከል ማጂሺያን ማረክ ደግሞ አንዱ ነው፤
ይህ ማጂሺያን የካንሰር ታማሚ ጨቅላ ልጁ የወደፊቱን የመተንበይ አቅሟን የሚያሳይ ትሪክ በማሳየት ዳኞችን በእንባ እያራጨ ጭምር የጎልደን በዘር ካገኙ ተወዳዳሪዎች መካከል ሌላኘው ነው፤በአሜሪካን ጎት ታለት በፈረንጆቹ 2014 በመቅረብ አስደናቂ ስራውን ያሳየች ድምጻዊ፤ ኮሜዲያን፤ ኢምፕረሽኒስት ናት ዳርሲ ሊን፤
ይህቺ ታዳጊ ከዚህ ቀደም ቴሪ ፌተር የተሰኘ ግለሰብ በአሜሪካ ጋት ታለንት ላይ አሻንጉሊትን በመጠቀም ያሳየውን የነበረው ቬንትሮሎኪውዝም በመስራት በእድሜዋ የማይጠበቅ አቅምን በማሳየት እና በማስደመም የጎልደን ባዛር አሸናፊ ሆናለች፡፡












