፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 20 2016| NBC ETHIOPIA-አዲስ አበባ ፖሊስ ተሽከርካሪ በሰረቀችው ግለሰብ ላይ ክስ ተመስርቶባት በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቧን አስውቋል፡፡
ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቢጫ ፎቅ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ መኪና ሰርቃ በፖሊስ ክትትል የተያዘችው መና ከበደ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ በመተላለፍ የማይገባትን ብልፅግና ለማግኘት ንብረትነቱ የግል ተባዳይ የሆነው የሰሌዳ ቁጥር 3 B 32912 አ/አ ተሽከርካሪ በመስረቋ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትባት ማደረጉን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ግለሰቧ ተለቃለች እንዲሁም ወንጀሉን ሳታውቅ ነው የፈፀመችው የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛል፡፡ የግል ተበዳይ መኪናቸው መሰረቁን ለፖሊስ ያመለከቱ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግለሰቧም ተሽከርካሪውን ለእረጅም ሰዓት ይዛ መሰወሯ ታሳቢ በማድረግና ድርጊቷም በማስረጃ በመረጋገጡ ዓቃቤ ህግ በተሽከርካሪ ስርቆት ክስ መመስረቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












