ያልተነገረላት ጀግኒት--ሸርሊ ቺሾልም
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 17 2016| NBC ETHIOPIA- ውልደቷ እ.ኤ.አ ህዳር 30, 1924 ዓ.ም ነበር፡፡ በዘመኑ የትኛውም አፍሪካዊ ያልፈተሰመውን ጀብዱ የፈጸመች እንስት ናት፡፡ ትምህርቷን የተከታተለችው በኒው ዮርክ ከተማ ነው፡፡ በብዙዎች ዘንድ ያልተነገረላት እና ያልተዘከረች ስትሆን በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ወንበር ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካ-አሜሪካዊ ሴት፡፡ ሸርሊ ቺሾልም
ሸርሊ ቺሾልም ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኃላ በኒው ዮርክ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ መስራት ጀመረች፡፡ ይህ አጋጣሚ የህይወቷን አዲስ ምዕራፍ የጀመረችበት እንዲሁም ወደ ታላቅ ህልሟ ያመራችበት ጎዳና ነው፡፡ ቺሾልም በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ወንበር ያገኘች የመጀመሪያዋ አፍሪካ-አሜሪካዊ ሴት መሆን የቻለች ሲሆን እ.ኤ.አ በ1964 በኒውዮርክ ግዛት መቀመጫ አገኘች፡፡ ከአራት ዓመታት በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች፡፡እጅግ ግልጽ እና ደፋር እንስት የሆነችው ቺሾልም ከሀገሪቱ የቴሌቪዝ ጣቢያ ጋር በነበራት ቆይታ አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ሴት ፕሬዝዳንት የሚያስፈልጋት ወቅት ላይ ትገኛለሽ ብለሽ ታስቢያለሽ በሚል ከጋዜጠኛው ለቀረበላት ጥያቄ የሰጠችው ምላሽ ዛሬም ድረስ ይታወሳል፡፡አሜሪካ ከየትኛው ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቅት ሴት ፕሬዝዳንት የሚያስፈልጋት እና በሴት ለመመራት ብቁ የሆነችበት ጊዜ ላይ ትገኛለች ብዬ አስባለሁ፡፡

በህልሟ ጽኑ የነበረችው ቺሾልም እ.ኤ.አ በአሜሪካ ለፕሬዚዳንትነት የተወዳደረች እና እጩ የሆነች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሆናለች፡፡ በዛሬው እለት በአሜረካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ተወዳዳሪ እጩ ሆኛለሁ። እኔ የጥቁር አሜሪካዊያን ተወካይ አይደለሁም፤ እኔም ጥቁር ነኝ በዚህም ኩራት ይሰማኛል፡፡ እኔ የእዚህ ሀገር የሴቶች ንቅናቄ ተወካይ አይደለሁም እኔም ሴት ነኝ፡፡ ይህም ኩራቴ ነው፡፡ እኔ ለመላው የአፍሪካ እና አሜሪካ ህዝቦች ተወካይ ነኝ፡፡
ለሴቶች፣ ለአናሳ ማህበረሰቦች፣ ለስደተኞች እና ለድሆች የእኩልነት መብት ለአመታት ታግላለች።በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ኢፍትሃዊ ድርጊቶች ላይ ቆራጥ አቋም በመያዝ እንዲሁም የጥቁር ሲቪል መብቶች እና የሴቶች መብት ደጋፊ በመሆኗ ትታወቃለች።“Fighting Shirley ሽርሊን” የሚል የቅጽል ስም የወጣላት እንስቷ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ ከ50 በላይ ህጎችን ለዓለም አስተዋውቃለች፡፡ በ1971 የኮንግረሱ ጥቁር ካውከስ (ሲቢሲ) መስራች እና አባል ሆናለች። ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ከወሰነች በኋላ ከቴሌቪዥን ክርክር መድረክ ላይ መታገዷን ተከትሎ የቴሌቪዥን ጣቢያውን መክሰሷ የህይወት ታሪክ መዝገቧ ያትታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1977 የዲሞክራቲክ ካውከስ ምክር ቤት ፀሐፊ ሆና ተመርጣለች፡፡ በኮንግረሱ ውስጥ ለሰባት ዙር ወይም ለ14 ዓመታት ያገለገለች ቆራጥ ሴት ናት ቺሾልም፡፡ እንደ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ሴናተር ኤልዛቤት ዋረን ላሉ የአሜሪካን አይነኬ የስልጣን መንበሮችን እንዲቆጣጠሩ ቺሾልም መልካም ዕድሎችን ከፍታለች፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ የመጀመሪያዋ ሴት ወይም አፍሪካዊ እንደሆነች መታወስ እንደማትፈልግ በተደጋጋሚ በምትገኝበት መደረኮች ላይ ተናግራለች።

“If they don’t give you a seat at the table, bring in a folding chair” ከቺሾልም አንደበት ላይ የማይጠፋ እና በየመድረኩ የምታነሳው ወኔ ሰጪ አባባሏ ነው፡:ቺሾልም እ.ኤ.አ. በ 1983 ከኮንግረስ ፓርቲ በጡረታ የተገለለች ሲሆን እ.ኤ.አ እ.ኤ.አ በጥር 1 2005 በ80 አመቷ ህይወቷ አልፏል፡፡በአሜሪካ ኮንግረስ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን Presidential Medal of Freedom የተሰኘውን የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት ህይወቷ ካለፈ ከአስር አመት በኋላ እ.ኤ.አ በ2015 ተበርክቶላታል፡፡












