፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 17 2016| NBC ETHIOPIA-6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡
ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መምራቱ የሚታወስ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በነገ ውሎው ረቂቅ አዋጁ የተመራላቸው የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት እንዲሁም የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የሚያቀርቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በማድመጥ አዋጁን መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡
በተጨማሪ ምክር ቤቱ የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












