፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 15 2016| NBC ETHIOPIA-የታይዋን ምክትል ፕሬዝዳንት ሂሲኦ -ቢኪም ሀገራቸው ራስን ከጥቃት የመከላከል ልምድ ከዩክሬን መማር እንዳለባት ተናገሩ፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቷ ይህንን ያሉት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሊ – ቺንግ ቻይና ፤ የግዛቴ አካል ናት በምትላት ታይዋን ላይ የመጠቅለል ፍላጎት እያሳየች እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ ነው፡፡

ታይዋን ከቻይና ለሚደርስባት የትኛውም ወረራ ራሷን ለመከላከል ወታደራዊ ስርዓቷን ማሻሻል እንዳለባትና ራስ ገዝ መሆኗን ማሳወቅ ትፈልጋለች ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቷ፡፡
ቴይፒ ከቤጅንግ ጥቃት ሊደርስብኝ ይችላል የሚል ስጋት እያደረባት እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡ ዘገባው የአር ቲ ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












