Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የዳርፉር ዳግም የዘር ማጥፋት ጉዞ

June 18, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-አመታትን ባስቆጠረ የእርስ በእር ጦርነት መቶሺዎች ለሞት ተዳርገዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ   ተፈናቅለዋል ፡፡ በጎሳ ግጭት እና በሰብአዊ ቀውሶች አስከፊ ታሪክ ያላት የምእራብ ሱዳኑዋ ዳርፉር ግዛት ፡፡

ዳርፉር እ.ኤ.አ. በ2000ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት የሆነ አስከፊ ግጭት አጋጥሟት እንደነበር የሚታዎስ ነው ፡፡

ታዲያ ዛሬ ላይ   ዳርፉር ያለፈውን አስከፊ ታሪኳ ረስታ እንደ አዲስ ወደ ሌላ የዘር ማጥፋት ወንጀል እያመራች ነው ሲል cnn ባወጣው መረጃ አመላከቷል ፡፡

የሱዳን ጦር እና የፍጥኖ ደራሽ ኃይሉ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከገቡ 14 ወራትን አስቆጥረዋል ፡፡ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ በዳርፉር ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግድያዎች ተባብሰዋል። በግጭቱም ከ14,000 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን እና ከ8 ሚሊየን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል ፡፡

ሁለቱ ሀይሎች ግዛቶችን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ፍልሚያ አሁን ላይ ወደ ኤል ፋሸር ተዘዋውሯል ፡፡  ግዛቷ የቀናት ጉዳይ እንጂ  በመሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ መራሹ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል  እጅ ልትወድቅ እንደምትችልም ተንታኞች ከሰሞኑ ያስታወሱት ከዚህ አንጻር ነው ፡፡

የጅምላ ጭፍጨፋ ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የመንደሮችን  ውድመትን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ግፍ  እና ከዘር የማጥራት ዘመቻዎች ጋር የተገናኙ የመብት ጥሰቶችን መፈጸማቸው ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ድርጅቶች ገልጸዋል ፡፡

ባለፈው ወር ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ኤል ፋሸርን መክበቡን ተከትሎ ቢያንስ 134 የከተማዋ ነዋሪዎች  ተገድለዋል ፡፡

በአሁን ወቅት በዳርፉር የተፈፀመው ጥቃት ዒላማ የተደረገበት ሁኔታ ፣ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ስልታዊ አካሄድ እና በአካባቢው ያሉ የጎሳ ግጭቶች እንዲሁም ቀድሞ የነበረው ታሪካዊ  ቁርሾ ዳርፉር ​​ወደ ሌላ አስከፊ  የዘር ማጥፋት እየተሻገረች እንደሆነ ማሳያዎች ናቸው ይላሉ ተንታኞች ፡፡

በአሁን ወቅት እየተፈፀመ ያለው ግፍ በአብዛኛው  በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ በነበረው የእርስ በእርስ ግጭት ተሳታፊ የነበሩ  ሀይሎች የሚሳተፉበት ነው ፡፡

ተመሳሳይ የጦር አዛዦች፣ ተመሳሳይ ጎሳዎች እና በዳርፉር የሚገኙ ተመሳሳይ የተጎጂ ቡድኖች (አረብ ያልሆኑ ማህበረሰቦች) በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑ ሌላኛው ማሳያ ነው ይላሉ ፡፡

2 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች የሚኖሩባት ኤል ፋሸር ማሳሊትን ጨምሮ አረብ ያልሆኑ ብሄረሰቦች በብዛት ይኖሩበታል ። ከተማዋ ባለፈው አመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አረብ ያልሆኑ ሰዎች የተገደሉባትን  ኤል ጂኒናን ጨምሮ ከሌሎች የዳርፉር አካባቢዎች የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን አስጠልላለች ።

በዚም የተነሳ ኤል ፋሸር  በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ቁጥጥር ስር ከገባች ተመሳሳይ ግፍ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል ፡፡

ግጭቱ ንጹሃን ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር እያገኘ ያለው ዓለም አቀፍ ምላሽ  በቂ አይደለም ተብሎ እየተተቸ ይገኛል ፡፡ በሱዳን ጦር ሃይሎች እና ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ  መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ  ተደረጉ አለም አቀፍ ጥረቶች አለመሳካታቸው የሚታወቅ ነው ። ምዕራባውያኑም ቢሆኑም ዜጎቻቸውን ከሱዳን ካስወጡ በኋላ ሱዳንን ጉዳይ ችላ ብለውታል በሚል ይወነጃጀላሉ፡፡

የሱዳን ጦርነት ከሌሎች አለም አቀፍ ግጭቶች ጋር ሲወዳደር በቂ ሽፋን እንዳልተሰጠው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ዮናህ ዳይመንድ ተናግሯል።

ሰላማዊ ዜጎችን የሚጎዳ፣ በሚሊዮኖች ላይ የረሃብ ሞት የሚያስከትል ግጭት እና እየተካሄደ ያለው የዘር ማፅዳት ተመሳሳይ ትኩረት የማይሰጥበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።

ይህ ትኩረት እጦት ሰብአዊ ጥረቶችን እንደሚያደናቅፍ ጠቁመው ጋዛ እና ዩክሬን እያንዳንዳቸው 30 በመቶ የሚሆነውን የሰብአዊ ድጋፍ ምላሽ እቅዳቸውን ሲያሳኩ 25 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው ሱዳን ከዚህ ገንዘብ ግማሽ ያህሉን ብቻ እንዳገኘ ጠቁመዋል።

አሜሪካ  ፣ እንግሊዝ እና ሌሎች ሀገራት ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ  የዘር ማጥፋት ዘመቻን እንዲያቆም በአጋራቸው በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያስችል አቅም  አላቸው ብለዋል።  በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን ካለው ጦርነት ጀርባ አለች መባሉ የሚታዎስ ነው፡፡

የሱዳን ጦረ በአብደል ፈታህ አልቡርሃን በመመራት በሌላ በኩል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ውስጥ ከገቡ ዓመት አልፏቸዋል፡፡

በ-የአብስራ ብርሃኑ

ShareTweetShare
Previous Post

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ተመስገን ጥሩነህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋትና የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ጎበኙ

Next Post

ኢትዮጵያ በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም እየተሳተፈች ነው

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢትዮጵያ በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም እየተሳተፈች ነው

ኢትዮጵያ በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም እየተሳተፈች ነው

የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር

የባህርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር

በትግራይ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው

በትግራይ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?