Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የስፔን ዲስፍሩታር ቅንጡ ሬስቶራንት

June 18, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-በርካታ የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ አገራት የቱሪስቶችን ፍሰት ለመጨመር ቅንጡ ሆቴሎችን ይገነባሉ፡፡ በሆቴሎቹ የሚደረጉ መስተንግዶዎችም ከመግቢያ አቀባበል ጀምሮ አንዳንዴ እንዲህም አለ እንዴ የሚያስብል ይሆናል።

ልዩ የፈጠራ ጥበብ የታከለባቸው ምግቦች በልዩ መስተንግዶአዊ አቀራረብ  ለተጠቃሚዎች የሚያቀርበውን ታዋቂውን የዓለማችን ቅንጡ እና ውዱ ሬስቶራንት እናስተዋወቃችሁ።

ይህ የምትመለከቱት የምግብ አይነት ነው ቢባሉ ያምኑ ይሆን? በዚህ ሬስቶራንት ምግብ ምግብ ብቻ ሆኖ አይቀርብም ጥበብ ታክሎበት እንጂ።

ደግሞ ለምግብ ምን የሚሉት መጠበብ ነው ሊሉ ይችላሉ ነገር ግን ዲስፍሩታር ሬስቶራንት በሚያቀርባቸው አስገራሚ የምግብ ፈጠራዎቹ የፈረንጅቹ 2024 ምርጡ የዓለማችን ሬስቶራንት መሆን ችሏል።

ወደ ዲስፍሩታር ሬስቶራንት ጎራ ያሉ እንደሆነ በምግቡ ጣዕም ተማርከው ብቻ ሳይሆን በምግብ አሰራር ጥበቡም ተደምመው ይወጣሉ።

ዲስፍሩታር  በስፔን ባርሴሎና የሚገኝ ከተለመደው የምግብ አሰራር ውጪ ለየት ያሉ አስገራሚ ፣እጅን በአፍ የሚያስጭኑ አንዳኔዴም ፈገግታን የሚጭሩ ምግቦችን የሚያገኙበት ቅንጡ ሬስቶራንት ነው።

ስፔን ጎራ ያሉ እንደሆነ  ወደዚህ አስገራሚ ሬስቶራንት ሳያቀኑ  መመልስ የማይታሰብ ስለመሆኑ እግራቸው ባ የረገጠ ሁሉ ይስማሙበታል። ዲስፍሩታር በስፓኒሽ “መደሰት” የሚል ትርጓሜን አለው።

ሬስቶራንቱ ይበልጡ የሚታወቀው ጣፋጭ ፣አስገራሚ እና ለየት ያሉ የምግብ አሰራሮችን ለተጠቃሚዎቹ በማቅረቡ ነው።

ቀደም ሲል በታዋቂው ኤልቡሊ ሬስቶራንት ውስጥ ይሠሩ በነበሩት በሼፍ ማትዩ ካሳናስ፣ ኦሪኦል ካስትሮ እና ኤድዋርድ ካትሩች እ.ኤ.አ. በ2014 ነው ዲስፍሩታር ሬስቶራንት የተከፈተው ።

በዲስፍሩታር ሬስቶራንት ሼፎች የምግብ አሰራር ጥበብን ብቻ ሳይሆን ፍጥነትንም ተክነውቦታል። ምግብ ዘገየ ብለው በፍጹም ስጋት አይገባዎትም ያዘዙት ምግብ በብርሀን ፍጥነት ያገኙታል።

ሬስቶራንቱ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ልዩ ፈጠራ የታከለበት ምግብ ከሚያቀርቡ ሬስቶራንቶች አንዱ  ነው። ሬስቶራንቱ ያልተጠበቁ የጣዕም ቅንጅቶች ያሏቸውን አዳዲስ የምግብ አሰራር እና አቀራረብ ያሳያል።

የስፔን ባህላዊ የምግብ አሰራርን ከዘመናዊ በማቀናጀት  የተለያዩ ቀለም እና ጣዕም ያላቸውን አዳዲስ የምግብ ፈጠራዎችን ያቀርባል።

ሬስቶራንቱ ከምርጥ ምግብ በተጨማሪ በሚያምር እና ዘመናዊ የመመገቢያ ክፍልም ፈጽሞ የሚታማ አይደለም ። እጅጉኑ ያማረ እና ትልቅ የመመገቢያ ክፍሎችም ያሉት ነው።

በ-ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

በ2014 በጀት አመት በዋና ኦዲተር ግኝት መመለስ ከነበረበት ከ443 ሚሊየን ብር የተመለሰው 11 በመቶ ብቻ ነው ተባለ

Next Post

ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚውል ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ አልዋለም ተባለ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚውል ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ አልዋለም ተባለ

ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚውል ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ አልዋለም ተባለ

በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀመረ

የ2024 የዓለም ምርጥ መዳረሻዎች

የ2024 የዓለም ምርጥ መዳረሻዎች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?