Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የዋተርጌት ቅሌት

June 18, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-ከ1969 እስከ 1974 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉትን ሪቻርድ ኒክሰን የፖለቲካ ህይወት ገደል የከተተው የዋተር ጌት ቅሌት በሚል የሚታወቀው ወንጀል የተፈጸመው ከዛሬ 52 ዓመታት በፊት በትላንትናው እለት በጎርጎሮሳውያኑ 1972 ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሰኔ 17፣ 1972 ማለዳ የዲሞክራቲክ ብሄራዊ ኮሚቴ ቢሮ በዘራፊዎች ተሰበረ ተባለ፡፡ መገኛው በዋሽንግተን ዲሲ ባለስልጣናት ለመኖሪያነት፣ ተቋማት ደግሞ ለቢሮነት በሚጠቀሙት በዝነኛውና ተመራጩ ዋተር ጌት ኮምፕሌክስ ነበር፡፡በወንጀሉ የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ካሜራዎች፣ የእስክሪፕቶ መጠን ያላቸው ሶስት አስለቃሽ ጋዝ መርጫዎች፣ የተራቀቁ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎችና ለወንጀሉ የሚያግዟቸው መሳሪያዎችን እንደያዙ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ፡፡

ከግለሰቦቹ መካከል ሶስቱ ኩባውያን፣ አንዱ አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ኩባዊ ሲሆኑ የቀረው ጄምስ ደብሊው ማክኮርድ ጁኒየር የተሰኘ የቀድሞ የሲአይኤ ወኪል ነበር፡፡ በተደረገው ተጨማሪ ምርመራ ጄምስ ማክኮርድ በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት እያስተዳደሩ የነበሩት ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ለዳግም የስልጣን ዘመን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚያስተባብረው አስመራጭ ኮሚቴ የደህንነት አስተባባሪ መሆኑ ተደረሰበት፡፡
“ፀረ-ኮምኒስቶች” ናቸው የተባሉት አምስቱ ተጠርጣሪዎች ከባድ የስርቆት ወንጀል እና የወንጀል መገልገያዎችን በመያዝ ወንጀልን ጨምሮ በስምንት ክሶች ተከሰሱ። ፕሬዝዳንቱ ቢያስተባብሉም የእሳቸው የቅርብ ሰው የሆኑና ከወንጀሉ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ 69 ሰዎች በወንጀሉ ተጠርጥረው የምርመራ አድማሱ ሰፋ፡፡

በእዚሀ መካከል ዘ ዋሺንግተን ፖስት ራሱ ነጩ ቤተ-መንግስት እና የፕሬዝዳንቱ ዳግም አስመራጭ ኮሚቴ ሳይቀር በድርጊቱ እጃቸው እንዳለበት ያረጋግጣሉ ያላቸውን ማስረጃዎች ይፋ አደረገ፡፡ ማስረጃው ኮሚቴው ለፕሬዝዳንቱ ዳግም መመረጥ የሚሰሩ በድብቅ የቀጠራቸው ሰላዮችና ለእዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ሚስጥራዊ ፈንድ መኖሩን ጭምር የሚያሳይ ነበር፡፡

እነኚህ መረጃና ማስረጃዎች ብሎም በጉዳዩ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እየሰፋ ቢመጣም ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰንን ለዳግም ስልጣን ከማሸነፍ አላገዳቸውም ነበር፡፡ ለእዛውም 60 ነጥብ 7 በመቶ በሆነ ከፍተኛ ድምጽ፡፡
በዋተርጌቱ ዝርፊያ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸውን ያመኑት አምስቱ ግለሰቦችን ጨምሮ በአጠቃላይ 48 ተጠርጣሪዎች ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት ተላለፈባቸው፡፡

የኒክሰን አስተዳደርም ቢሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን ሲጥር እንደነበር ራሱ ፍርድ ቤቱ ሳይቀር ኮንኖ ነበር፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጥርጣሬ አይን እየታዩና አንዱ አንዱን ተጠያቂ እያደረገ ጉዳዩ በቀላሉ መቋጫ አጣ፡፡
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ባይገለጽም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ እና የነጩ ቤተ-መንግስት ሁለት ከፍተኛ አማካሪዎች ስራቸውን ለቀቁ፣ አማካሪውም ከስራቸው ተባረሩ።

የኒክሰን ዳግም አስመራጭ ኮሚቴ በፖለቲካዊ ስለላ፣ በህገወጥ ጥቅማጥቅሞች እና ሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ መሳተፉን የሚገልጹ ማስረጃዎች ተጋለጡ፣በነጩ ቤተ-መንግስት ትልቅ ውጥረት ሰፈነ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ከቤተ-መንግስቱ ሰራተኞችና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቤተ-መንግስቱ ያደረጓቸው ንግግሮች ቅጂ ላይ ምርመራ ቢደረግም ሃቁ ሊደረስበት አልቻለም፡፡ በጊዜ ሂደት ፕሬዝዳንት ኒክሰን በህዝቡ ዘንድ ያላቸው ተዓማኒነት እየተሸረሸረ ሄደ፡፡
የተወካዮች ምክር ቤቱ የዳኝነት ኮሚቴ በፕሬዚዳንት ኒክሰን ላይ በፍትህ ማፈን፣ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም እና በክስ ሂደቱ ላይ እንቅፋት በመፍጠር በሚል ክስ አቀረበበት፡፡

ክሱ ምክር ቤቱ አንድ የመንግስት ባለስልጣንን ከስልጣኑ ለማንሳት የሚወስደው የመጀመሪያው ወሳኝ እርምጃ ነው። አማራጭ ያጡት ፕሬዝዳንቱ ቅጂዎቹን አስረከቡ፡፡
ይሄኔ ፕሬዝዳንቱ የዋተርጌቱ ምርመራ እንዲቆም እንዲያደርግ ለFBI ትዕዛዝ ሲሰጡ የሚያሰማን ድምጽ ቅጂዎቹ አጋለጡ፡፡ ከአራት ቀናት በኋላም ፕሬዝዳንት ኒክሰን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ስልጣን የለቀቁ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ሆነው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ፡፡ ተተኪያቸው ፕሬዝዳንት ጄራልድ ፎርድ ከማንኛውም የወንጀል ክስ ይቅርታ አድርገውላቸው ከቅጣት ተረፉ፡፡ በዋተርጌቱ ቅሌት በአጠቃላይ 69 ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸው 48ቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።ከዛሬ 52 ዓመታት በፊት ልክ በትላንትናው እለት የተፈጸመውን የዋተር ጌቱን ቅሌት ከታሪክ ማህደር መዘን እንዲህ አስቃኘናችሁ፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

Next Post

ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን በመቅረፅ ሂደት ውስጥ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው?

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን በመቅረፅ ሂደት ውስጥ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው?

ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን በመቅረፅ ሂደት ውስጥ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው?

ኢትዮጵያ ነፃ ኢኮኖሚ ይኖራት ዘንድ መገናኛ ብዙሃን ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ነፃ ኢኮኖሚ ይኖራት ዘንድ መገናኛ ብዙሃን ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እያዳመጠ ነው 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እያዳመጠ ነው 

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?