፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 10 2016| NBC ETHIOPIA-በአዲስ አበባ የሚገኙ 35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሂዱ ማገዱን የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሰታወቀ።
ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ የትምህርት ተቋማትንም ይፋ አድርጓል። የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛዉ ገብሩ እንደገለጹት፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን ባደረገዉ ቁጥጥር የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙና የትምህርት መመሪያዎችን ያላሟሉ 35 የግል ይዞታ ያላቸዉ ትምህርት ቤቶች ላይ እገዳ ጥሏል።
ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች መካከልም የካ፣ ልደታ ጉለሌና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች፣የቅዱስ ሚካኤል አምስት ትምህርት ቤቶች፣ የካ አፖሎ ትምህርት ቤት ይገኙበታል።
የቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች የስያሜ ለዉጥ በማድረግ ለመቀጠል በመጠየቁም ጉዳዩ እየታየ መሆኑ ተገልጿል።
ዕገዳ በተጣለባቸዉ ትምህር ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በመኖረያ አቅሪያቢያቸዉ በሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንዲስተናግዱ ይደረጋል ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












