Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የማያውያን ስልጣኔ ከተማ ቱሉም    

June 13, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 06 2016| NBC ETHIOPIA-ጥቂት በግንብ ከታጠሩ ከተሞች ውስጥ አንዷ ናት ፡፡ ባሏት የስነ ምድር ምርምር ስፍራዎች እና የባህር ዳርቻዎቿ የበርካታ ጎብኚዎችን ቀልብ ትገዛለች ፡፡ የሜክሲኮዋ ቱሌም ከተማ ፡፡

ከተማዋ ከ820 አመታት በፊት በማይውያን ስልጣኔ እንደተገነባች ይነገራል ፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በእስፓኒሽ ወረራ ምክንያት ከተማዋን የመሰረቷት የማይ ህዝቦች ለቀው እንደወጡ እና  ለበርካታ አመታት ተረስታ ከቆየች በኋላ በ1840 ፍሬድሪክ እና ጆን ሎይድ በተባሉ ግለሰቦች ምክንያት ዳግም እንደተገኘች መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡  

ለብዙ ግዜያት ከሩቅ ቦታዎች ለሚመጡ እና ለአካባቢው ሰዎች  እንደ ዋና የንግድ ጣቢያ ሆና አገልግላለች። ጥጥ፣ካካኦ ፣ትምባሆ እንዲሁም ለሌሎች  በርካታ ነገሮች በስፋት ይነገድባት እንደነበር ይነገራል ፡፡

ጥንታዊ ታሪኳ እና አሁን ላይ ያላት ውብ ድባብ ተጣምረው በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን አድርገዋታል፡፡ ከተማዋ በሜክስኮ በብዛት ከሚጎበኙ ስፍራዎች  ቀዳሚውን  ቦታ ትይዛለች ፡፡   

ከመዝናናት ባለፍ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ  በአርኪኦሎጂ ስፍራዎቿ በታሪክ አድናቂዎች ዘንድ ከምንግዜውም በላይ  ተወዳጅ እየሆነች መታለች።

ከአሰልቺ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ዞር ብሎ በሞቃታማ ገነት ውስጥ ለማሳለፍ ለሚፈልግ ጎብኚም ቀዳሚ ምርጫ ናት ፡፡

ወደ ቱሌም ከተጓዙ ከአስገራሚ ተፈጥሯዊ ጸጋዋ ጀምሮ አዲስ የሚታይ እና የሚከወን ነገር አያልቅም ይባላል፡፡ ቱሌም በቀድሞ ዘመን  የንግድ ማዕከል ከመሆኑዋ በተጨማሪ የማያውያን የአምልኮ ስፍራ  እንደነበረች በከተማዋ በቀድሞው ዘመን የተገነቡት ቤተ መቅደሶች እና በተለያዩ ስፍራ በግንቦች ላይ የተቀረጹት ምስሎች ያስረዳሉ፡፡

በከተማዋ ከ60 በላይ ጥንታዊ ህንጻዎች ሲኖሩ ኤል ካስቲሎ ፣የፍሬስኮስ ቤተ መቅደስ እና Descending God ይተሰኙት ደግሞ በጥብቅ ከሚጠበቁት ውስጥ ናቸው ፡፡

ቱሌም ለጎብኚዎች ምቹ ከመሆኑዋም ባሻገር የበርካታ እንስሳት መኖሪያ ናት ፡፡  በጥቂት ቦታዎች ብቻ የሚገኘው ጃጉዋርን ጨምሮ ፣ኤሊ፣ ጦጣ፣ አጋዘን ፣ፓሮት እና የተለያዩ እንስሳት መኖሪያ ናት፡፡

ከቱሌም ከተማ ወጣ ብሎ በደን ውስጥ የሚገኘው አዙሊክ ኡህ ሜይ ወይም የጥበብ ከተማ ሙዚየም ለጥበብ ሰዎች እና ለሀሳብ ፈጠራ ምርጡ ስፍራ ነው ፡፡

ወደ ቱሌም የተጓዘ ጎብኚ በተንጣለለው እና በማራኪው ባህር ዳርቻ መዝናናት ፣ በውሃ ላይ የሚከወኑ  ስፖርታዊ መዝናኛዎች  እና በከተማዋ የሚገኘውን ትልቅ ፒራሚድ መውጣት ሊዝናኑባቸው የሚችሉበት ጥቂት ስፍራዎች ናቸው፡፡

Playa Paraiso ፣Play Ruinas እና አኩማል በቱሌም ከሚገኙ ውብ የባህር ዳርቻዎች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው፡፡ ታዲያ ይችን በተፈጥሮ ጸጋ እና በሰው ሰራሽ ታሪክ የበለጸገች ከተማን ለመጎብኘት ህዳር እና ታህሳስ ተመራጭ ወቅት ነው ፡፡

በአሁን ወቅት በየጊዜው ወደከተማዋ የሚጓዙ ጎብኚዎች ቁጥር ከምንግዜም በላይ እየጨመረ ነው ፡፡ በአመት በአማካኝ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ወደ ከተማዋ እንደሚጎርፉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በ-የአብስራ ሚሊዩን

ShareTweetShare
Previous Post

1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ተመለሱ

Next Post

በምክክር ትዳን ሀገር

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
በምክክር ትዳን ሀገር

በምክክር ትዳን ሀገር

የቡል ፌስቲቫል በስፔን

የቡል ፌስቲቫል በስፔን

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?