፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 04 2016| NBC ETHIOPIA- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በዛሬው እለት በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀመረ።

ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ182 የፈተና ጣቢያዎች 86,672 ተማሪዎችን እንዲሁም 2,200 ፈታኞችን ፣ 700 ሱፐር ቫይዘሮችን ጨምሮ 182 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን በማሳተፍ በዛሬው እለት መሰጠት ጀምራል።

ተማሪዎች በጠዋቱ የፈተና ጊዜ አማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎችን እንደሚወስዱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












