፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 04 2016| NBC ETHIOPIA- በሩሲያ ፌዴሬሽን ኒዥኒ ኖቭጎሮድ በሚካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት አምባሳደር ታዬ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር ታዬ ከቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂያዊ አጋርነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
አምባሳደሩ ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም መሰረት ባደረጉ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ሁሉቱ የስራ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተፈረሙ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነቶችን ወደ ተግባር መቀየር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውም ተጠቅሷል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












