፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል::
ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
አዋጁ ከዚህ ቀደም በመንግስት የግዥና ንብረት አሰተዳደር ሂደትና ትግበራ ወቅት በአፈፃፀም ሲያጋጥሙ የነበሩ እና ለመልካም አሰተዳደር ችግር ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ የአሰራር ጉድለቶችን ለማረም ወሳኝ እንደሆነ ተገልጿል::
አዋጁ የመንግሥት የግዢና ንብረት አሰተዳደር ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር መራመድ እንዲችል ለማድረግና የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማበረታታት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ስለመሆኑም ተጠቁሟል::
አዋጁ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይም ተፈፃሚ እንደሚሆን ተጠቁሟል:: በመጨረሻም የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1333/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












