Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የፕሪዝን ብሬክ አስገራሚ እውነታዎች

June 10, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ 03 2016| NBC ETHIOPIA- የምን ጊዜም ተወዳጅ እና ተናፋቂ የዓለማችን ምርጡ ተከታታይ ድራማ ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማሙበታል። ከብዙዎች አእምሮ ሳይጠፋ እንደተወደደ ዓመታትን መዝለቅ ችሏል። ፕሪዝን ብሬክ

ፕሪዝን ብሬክ እ.ኤ.አ ከ2005 እስከ 2017 በ 5 ተከታታይ ምዕራፎች የቀረበ የአሜሪካ ተከታታይ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ድራማ ነው።የድራማው ታሪክ የሚያጠነጥነው ሊንከን ቡሮውስ እና ማይክል ስኮፊልድ የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች የህይወት ታሪክ ላይ ነው።ሊንከን ቡሮውስ ባልፈጸመው ወንጀል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ወደ ወህኒ ይወረወራል ። ማይክል ስኮፊልድም እቅድ በመንደፍ ወንድሙን ነጻ ለማውጣት ሲሞክር ያስመለክተናል።

ፕሪዝን ብሬክ የወንድማማችነት ትስስርን፣ ወንድማማቾቹ ከእስር ለመወጣት የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ጉዞ እና ያልተጠበቁ ሴራዎች በማስመልከት ልብ አንጠልጣይ በሆነ ትዕይንት ተመልካቾችን እያጓጓ የታየ ዘመን አይሽሬ ድራማ ነው።

የድራማው ዋና ገጸ-ባህሪያትም በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ እና አይረሴ ሆነው አሁንም ድረስ ይታወሳሉ።ስለ ፕሪዝን ብሬክ ተወዳጅ ተከታታይ ድራማ ያስገርማሉ ያልናቸውን እውነታዎች በጥቂቱ ልናስመለክታችሁ ወደድን።

እ.ኤ.አ ከ2005 እስከ 2006 ባሉት ጊዜያት በመላው ካናዳ በመጀመሪያው ምዕራፍ ብቻ ከ18 እስከ 49 የእድሜ ክልል ባሉ 1.4 ሚሊዮን ተመልካቾች እንደታየ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በወቅቱ በሀገሪቱ ከነበሩ ከ20 የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎችም ቀዳሚውን ደረጃ ተቆናጦ ነበር፡፡

በአውስትራሊያ በእያንዳንዱ ምዕራፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጥበብ አፍቃሪያን ተከታትለውታል፣ በፈረንሳይ እ.ኤ.አ ከነሃሴ 2006 ጀምሮ መታየት የጀመረው ፕሪዝን ብሬክ 5.5 ሚሊዮን  ተመልካቾችን አግኝቷል፣ በመላው ዓለምም በበርካቶች በመታየት ከቀዳሚዎቹ መካከል መሆን ችሏል፡፡

ፕሪዝን ብሬክ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ አጠቃላይ ከ 100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰሰ የተደረገበት ድንቅ ድራማም ነው።

በወቅቱ ፕሪዝን ብሬክ ተከታታይ ድራማ ሲተላለፍ የማይክል ስኮፊልድ ገጸ ባህሪይ የነበረው ከእስር የማምለጫ እቅድ በእውነተኛው ዓለም ላሉ ታሳሪዎች  አነቃቂ  ሊሆን ይችላል በሚል አሜሪካ ስጋት ገብቷት ነበር፡፡ በስጋትነት ከመመልከት ባሻገር በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 13 እስር ቤቶች ላይ እንዳይታይ እስከመከልከል ደርሳ ነበር፡፡

የፕሪዝን ብሬክ ተከታታይ ድራማ ገጽ ባህሪያት የሆኑት ሁለቱ ወንድማማቾች ለድራማው የተመረጡት ቀረጻ ለመጀመር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት መሆኑ ብዙዎች ያሰገረመ ክስተት ነው።

የፊልሙ መለያ እስከመሆን የደረሰው የማይክል ስኮፊልድ ንቅሳት በጥንቃቄ የተነደፈ እና ትክክለኛ እንዲመስልም  በርካታ ባለሙያዎች ተረባርበውበታል፡፡

የእስር ቤቱን እያንዳንዱን መውጫ መግቢያ የያዘው የማይክል ስኮፊልድ ንቅሳትም  ጊዜያዊ በመሆኑ ቀረጻ በሚኖር ጊዜ ሁሉ እንደገና የሚሰራ ነበር። ይህም ድራማው ብዙ እንደተለፋበት አንዱ ማሳያ ስለመሆኑ ይነጋራል፡፡

የፕሪዝን ብሬክ ሌላኛው አስገራሚ እውነታ የፕሮዳክሽኑ ቡድን እውነተኛ የሆነ ስሜትን ለተመልካች ለማጋባት ድራማው የተሰራው በእውነተኛ ወይህኒ ቤት ሲሆን በአሜሪካ የወንጀል ታሪክ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ በታሰረበት እና እ.ኤ.አ በ 2002 በተዘጋው ጆሌት ወይኒ ቤት ነው።

ፕሪዝን ብሬክ ተከታታይ ድራማ እ.ኤ.አ በ 2005 የፒፕል ቾይስ አዋርድን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን መውሰድ ችሏል። በራሚን ድጃዋዲ የተቀናበረው የፕሪዝን ብሬክ ተከታታይ ድራማ ማጀቢያ ሙዚቃ እጅግ ተወዳጅነት ማትረፍ ያቻ ተወዳጅ ሙዚቃ ነው።

በ-ሃይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

ዩክሬን ሩሲያ ላይ ጥቃት ከፈተች

Next Post

መጋኛ የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)?

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
መጋኛ የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)?

መጋኛ የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)?

የስፖንጅ ከተሞች

የስፖንጅ ከተሞች

በናይጄሪያ የተፈጸመ ጥቃት 

በናይጄሪያ የተፈጸመ ጥቃት 

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?