፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 30 2016| NBC ETHIOPIA-ከመላው አለም እውቅናን ለመቀዳጀት ለየት ያለ ሁነትን በመፈጸም እጅ በአፍ ለማስጫን አስደናቂ ድርጊቶችን ሲከውኑ መመልከት የተለመደ ነው፡፡
እነዚህን ሁነቶች ደግሞ ሰዎች ቢመለከቷቸው ሊያዝናኑ እና ለእርካታ እድል በሮችን ሊከፍቱ ይችላሉ በሚል የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ በክብር ለዘመን ይሻገሩ ዘንድ ይመዘግባል፡፡
ለዛሬ በአለማችን ላይ በግዝፈታቸው በጊነስ ቡክ ኦፍ ወርልድ ሪከርድስ ከተመዘገቡ ትልልቅ የምግብ አይነቶች ጥቂቶቹን እንስቃኛችሁ፡፡
1.የአለም ግዙፍ ኬክ

በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ኬክ ምን አልባትም በተለያዩ የሰርግ እና ሌሎች ስነስርአቶች ላይ ግዙፍ ሆኖ ተመልክተው ያውቁ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የአለማችን ግዙፉ ኬክ ርዝመቱና ግዝፈቱ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል አስበውት ያውቃሉ፡፡
የአለማችን ግዙፉ እና ረዥሙ ኬክ የተሰራው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በደቡባዊ ህንድ ውስጥ ነው፡፡
በጥር 16 2020 በደቡባዊ የህንድ ግዛት የሚኖሩ ከ1500 የሚልቁ ሼፎች ህብረት የሆነው Bakers Association Kerala (BAKE) አማካኝነት በመሰባሰብ ያዘጋጁት ሲሆን 6.5 ኪሎሜትር ወይንም 4 ማይልስ ርዝማኔ አለው፡፡
ከዚህ ቀደም በ2008 አመተ ምህረት በኢንዶኔዢያውያን የተሰራውን ግዙፉን ኬክ ለመብለጥ ታስቦ ለህንዶቹ ትሪሹር ፌስቲቫል ነው የተዘጋጀው፡፡
ቫኒላ፤ የቾኮሌት እና ሌሎች የኬክ መስሪያ ግብአቶችን በመጠቀም የተሰራው ይህ ኬክ 27 ቶን ክብደትም አለው ተብሎለታል፡፡ የአለም ግዙፍ ኬክ ተብሎም በድንቃድን መዝገቡ ሰፍሯል
2. ግዙፉ ፒዛ

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2023 በአሜሪካን ሎስ አንጀለስ ውስጥ የተሰራው ግዙፉ ፒዛ ሌላኛው በጊነስ ቡክ ኦፈ ወርልድ ሪከርድ ከተመዘገቡ ግዙፍ የምግብ አይነቶች ሌላኛው ነው፡፡
1296.72 ሜትር ስኬር ወይንም 13 ሺ 990 ጫማ ርዝማኔ ያለው የአለማችንን ግዙፉን ፒዛ በመስራት ኤርራክ የተሰኘው ግለሰብ እውቅናን ማግኘት ችሏል፡፡
ኤርራክ የተለያዩ ሰዎችን በማስተባበር የሰራው ይህ ፒዛ 6 ሺ 193 ኪሎግራም ወይንም 13 ሺ 653 ፓውንድ ሊጥ ፤2ሺ 2244 ኪሎግራም ወይንም 4ሺ 948 ፓውንድ ስዊት ማሪና ሶስ 3ሺ 992 ኪሎ ወይንም ቺዝ 630,496 pepperoni slices በውስጡ በመያዝ የአለማችን ትልቁ ፒዛ በመሆን በጊነስ ቡክ ኦፍ ወርልድ ሪከርድስ ተመዝግቧል፡፡
3. የአማችንን ትልቁ በርገር

ከተለመደው የዳቦ ቅርፅ እና መጠን እንዲሁም ግብአቶች ተለይቶ ብዙዎቻችን ተመልክተነው ላናቅ እንችላለን በርገርን፡፡
ነገር ግን በፈረንጆቹ 2017 በሀገረ ጀርመን ቮልፍግንግ ሊብ፤ ቶም ሬይቸነደር፤ ሩዲ ዲየትል፤ ጆሴፍ ዜልነር የአማችንን ትልቁ በርገር እውን እንዲሆን አድርገዋል፡፡
1ሺ 164.2 ኪሎ ግራም የሚዘንው ይህ የአለማችን ትልቁ ሀምበርገር የተሰራበት እያንዳንዱ ግብአት ለምሳሌ እንደ ስጋ፣ ቺዝአትክልቶች እና መሰል ግብአቶች ከ 300 ፓውንድ በላይ ይመዝናሉ፡፡
ይህ ከአንድ ሺ አንድ መቶ ኪሎግራም በላይ የሚመዝን በርገር የአለም ግዙፉ በርገር ተብሎ ነው እስከዛሬ ተወዳዳሪ ሳይገኝለት በመዝገቡ ሰፍሮ የቆየው…
4.ግዙፉ ቸኮሌት

12ሺ ፓውንድ የሚመዝነው ከዛሬ 12 አመታት በፊት ለአለም የቀረበው ግዙፉ ቸኮሌት በአሜሪካን ቺካጎ ውስጥ የተሰራው ነበር፡፡
ቸኮሌቱ 3ጫማ ከፍታ፤ 4ጫማ ስፋት እና 21ጫማ ርዝመት አለው፡፡1200 ፓውንድ አልሞንድ፤ 5ሺ500 ስኳር እንዲሁም ከ1 ቶን ካካኦ ቅቤ የተሰራ ነበር፣ በጊነስ ቡክ ኦፍ ወርልድ ሪከርድስ ላይ ክብረወሰኑን በመቆጣጠር ለረዥም ግዜያት ሊቆይ ችሏል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












