፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 29 2016| NBC ETHIOPIA-ማራኪ በሆኑ መዝናኛ ስፍራዎች ሰብሰብ ብሎ ቡና መጠጣት፣ ወደ ሱቆች ጎራ ብሎ መገበያየት እንዲሁም በምግብ ቤቶችና በሕዝባዊ ቦታዎች እንደመዘዋወር ያሉ ሁነቶች ሰዎችን ሃሴት እንደሚሰጡ ድርጊቶች ይታያሉ ፡፡
ነገር ግን ለአሥርት ዓመታት የቆየ መኪናን ማዕከል ያደረገ የሀገራት ፖሊሲ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከተሞች ለእግረኛ ምቹ የሆኑ ጎዳናዎች እንዳይኖሯቸው እንዳደረጉ “The ABC of Mobility” የተሰኘ አዲስ ጥናት ይፋ ማድረጉን ሲኤንኤን አስነብቧል፡፡
አንድ ከተማ በይበልጥ እየሰፋና እየበለፀገ ሲሄድ ለእግረኛ ምቹ የመሆኑ ሁኔታው እየቀነሰ እንደሚሄድ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ዘ ኢኮኖሚስት ባወጣው ጥናት ደግሞ ከዚህ የተለዩ ብዙ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ይናገራል፡፡ ጥናት ከተካሄደባቸው 794 ከተሞች መካከል የሞዛምቢኳ የወደብ ከተማ ኩዊልማኔ ለእግረኛ ምቹ ከሆኑ ስፍራዎች ውስጥ ተጠቅሳለች፡፡ ጥናቱ ባስቀመጠው ሌሎች በምርጥ 10 ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች በስፔን የሚገኙ አራት ከተሞችን ጨምሮ በአውሮፓ የሚገኙ ከተሞችን ያካተተ ነው፡፡

በኔዘርላንድ የኡትሪክት መተላለፊያ እንዲሁም በቱሪስቶች ተመራጭ የሆነችው አምስተርዳም ሰዎች ረጋ ብለው ለመንቀሳቀስ ከሚመርጧቸው ከተሞች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። በሰሜናዊ ስፔን የምትገኘው የቢልባኦ የወደብ ከተማ በፍራንክ ጌሪ ንድፍ በተሠራው የጉግገንሃይም ሙዚየም የምትታወቀው እንዲሁም የሮማውያን ካቴድራሎችም በጥናቱ በመልካም ተመላክተዋል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ Alpine region of Tyrol ጣሊያን ከኦስትሪያ ጋር የምትገናኝበትን ክልል ለእግር ጉዙ አመቺ ሲል አሞካሽቷል፡፡ታዲያ በሲኤንኤን ይፋ የተደረገው “The ABC of Mobility” የተሰኘው ጥናት አሜሪካን በዓለም ላይ በእግር ለመጓዝ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ዝቅተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡
ጥናቱ ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው በከተማና ከከተማ በራቁ ስፍራዎች የሕዝብ ትራንስፖርት ወይም መኪናን መጠቀም ትተው በእግር ሲጋዙ ከነበሩ ወደ 850 ሚሊዮን ከሚጠጉ ሰዎች በተገኘ ዳሰሳ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጥናቱ እንዳመለከተው ከተሸከርካሪ ለመራቅና በእግሩ ለመጓዝ ለሚፈልግ አሜሪካ ምቹ ሆና አልተገኘችም፡፡ በጥናቱ ጥያቄ ከቀረበላቸው ሰዎች መካከል በአሜሪካና በካናዳ 92 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች አዘውትረው በመኪና ይጓዛሉ። ከ4 በመቶ ያነሱት ደግሞ በእግርና በብስክሌት እንደሚጓዙ ጥናቱ አመላክቷል፡፡

ዘ ኢኮኖሚስት እንደጠቆመው ከሆነ 100 የማይሞሉ በእግር መጓዝ የሚቻልባቸው ከተሞች የሚገኙት በሰሜን አሜሪካ ነው፤ እነዚህ ከተሞች ባለፉት አሥርተ ዓመታት የመኪና ማዕከላዊ ፖሊሲ ሲተገበርባቸው እንዲሁም መንግሥት የገንዘብ ድጎማ ሲያደርግ በመቆየቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
በአለም ላይ ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው ግንኙነት እየቀነሰ መምጣቱ አዳዲሲ ቴክኖሎጂዎች ቶሎ ቦታ እንዲያገኙ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ግን በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ በርካታ ማህበረሰቦች አሁንም ከመሬት ጋር ያላቸውን ቁርኝት መተው አይፈለጉምና እነሱንም ያማከሉ አሰራሮች ተገቢ ናቸው ሲሊ ጥናቱ አስረድቷል፡፡ በተለይም የትራፊክ ጭንቅንቁኑ, ጫጫታውን እና የአየር ብክለቱን የጠሉ መሸሸጊያ ይፈልጋሉ፡፡ ታዲያ በዚህን ጊዜ ዘመኑ ካመጣቸው መልካም እድሎች ሳይርቁ ለመቆየት ንፁህ አየር ያለባቸውና ለእግር ጉዞ አመቺ የሆኑ ስፍራዎች ሊታሰብባቸው ይገባል፡፡












