፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 2016| NBC ETHIOPIA-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራምን በማዘጋጀት በዘርፉ ልዩ ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ታዳጊዎችን ሊያወዳድር መሆኑን አስታውቋል። ተቋሙ ከግንቦት 16 እስከ 30 ባሉት ቀናት በመላው የሀገሪቱ ከፍሎች የሚገኙ እድሜያቸው ከ11ዓመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በመመዝገብ ቻሌንጁን መቀላቀል ይችላሉ ብሏል።
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ቢሻው በየነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በቂ የተማረ የሰው ሀይል ባለመኖር የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ሰዎችን በመመልመል ዘርፉን እንዲቀላቀሉ ለማስቻል በማለም ቻሌንጁ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በሳይበር ደህንነት፣ኢሮስፔስ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑዘርፎች የቻሌንጁ የትኩረት መስኮቹ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አንስተው ተመዝጋቢዎች https://talent.insa.gov.et የተሰኘውን የተቋሙን ዌብሳይት በመጠቀም ምዝገባቸውን ማከናወን እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












