፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 2016| NBC ETHIOPIA-በፓፓዋ ኒው ጊኒ በደረሰ የመሬት መንሸራትት የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተገለጸ፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በስድስት መንደሮች የተጠፈረው መሬት መንሸራተት አደጋ በነዋሪዎች ላይ ስጋት ጋርጧል፡፡

በፓፓዋ ኒው ጊኒ ሰሜን ኢንጋ ከፍተኛ ቦታዎች የሚኖሩ አንድ መቶ መንደሮች በመሬት መንሸራትተ አደጋው ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምስ ማራፔ የነፍስ አድን ሰራተኞችን ወደ ቦታው እንደላኩ ተናግረዋል ፡፡
እስካሁን በአደጋው ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ በአሀዝ የታወቀ ነገር የለም ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












