፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 2016| NBC ETHIOPIA-አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖር የቀለም ትምህርት በተሳለጠ ሁኔታ እንዳይዳረስ ፈተና ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል፡፡ ይህንን በመገንዘብ የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ ከተገነቡ ምርጥ የአይነስውራን ትምህርት ቤቶች ለዛሬ የተወሰኑትን እንንገራችሁ፡፡
በሀገር አሜሪካ የመጀመሪያው የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት እንደሆነ ይነገርለታል፡- Perkins School for the Blind ትምህርት ቤት ፡፡

ምስረታውን እ.ኤ.አ በ1829 ያደረገው ትምህርት ቤቱ፣ ወደስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በዋናነት የእይታ ችግር ያለባቸው በተጨማሪም የመስማት ችግር እንዲሁም ተጨማሪ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህጻናት ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከአሜሪካ ባሻገር በሌሎች 100 ሀገራት አካል ጉዳት ያለባችው ህጻናት እና ወጣቶችን ለማብቃት እየሰራ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ እኩል እንዲራመዱ የቴክኖሎጂ ማዕከል ገንብቶ በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር የግብረገብ ፣ የስነ ልቦና እና የተለያዩ ማህበራዊ ትምህርቶች ይሰጣል፡፡ሌላኛው በአሜሪካ የሚገኘው Indiana School For The Blind የተሰኘው ትምህርት ቤት ሲሆን፣

በተመሳሳይ እይታ ችግር ያለባቸውን እና ሌሎች አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ተቀብሎ የሚያስተምር ትምህርት ቤት ነው ፡፡ ትምህርት ቤቱ ከሌሎቹ በተለየ የራሱን የትምህርት ካሪኩለም ቀርጾ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ እድሜያቸው ከ ሶሰት እስከ 22 አመት ያሉ ህጻናትና ወጣቶችን ተቀብሎ ከ መዋለህጻናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ያስተምራል፡፡ የትምህርት አሰጣጡ በአብዛኛው የተግባር እንቅስቃሴን ያካተተ ከመሆኑ በዘለለ በከፍተኛ በሰለጠኑ መምህራን የሚሰጥ ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ፣ ተማሪዎች ማህበራዊ እና የእርስበእርስ ግንኙነት ለማጎልበት ዋናን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ ፡፡ ለተማሪዎች ምቹ የሆነ ስፍራም የተመቻቸለትመሆኑ ከእውቅ የአይነስውራን ትምህርት ቤቶች እንዲመደብ አድርጎታል፡፡
በሀገረ ህንድ የሚገኘው Sri Rakum School for the Blind ትምህርት ቤት፡፡

ትምህርት ቤቱ ከማዋለ ህጻናት ጀምሮ እስከ ድህረ ምረቃ ያለምንም ክፍያ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያገለግል እውቅ የአይነ ስውራን ትምህርት ቤት ሲሆን፣ የትምህርት አሰጣጡም ከመሰረታዊ በብሬይል ማንበብ ጀምሮ የተለያዩ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው፡፡ በርካታ ዜጎቿ የእይታ ችግር ካለባቸው ሀገራት ከቀዳሚዎቹ በምትጠቀሰው ህንድ 247 የአይነ ስውራን ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን፣ Sri Rakum School for the Blind ከቀዳሚዎቹ መካከል ነው፡፡
Texas School For The Blind and Visually Impaired ትምህርት ቤት፡፡

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት የሚገኘው ትምህርት ቤቱ፣ በአሁን ወቅት ከ 11ሺ በላይ ማየት እና መስማት
የተሳናቸው ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡ የትምህርት
አሰጣጥ ሂደቱም መደበኛ የትምህርት ስርአቱን ጨምሮ በበይነ መረብ የሚሰጥ ከመሆኑ ባለፈ የተለያዩ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው ፡፡ ትምህርት ቤቱ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን በመስራት
ላይ ሲሆን፣ በሚሰጠው አገልግሎት እውቅናን በማትረፍ ቤቶች የአይነስውራን ትምህርት መሆን ችሏል፡፡ወደ አህጉረ አፍሪካ ስንመጣበደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ፕሪንሾፍ የአይነስውራንትምህርት ቤት በጉልህ ይታወቃል፡፡ ትምህርት ቤቱ በከፊል ማየት የተሳናቸውን እና ሙሉ በሙሉ እይታቸውን ያጡ ተማሪዎችን ያካተተ
ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከመሰረት ትምህርትእስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር ሲሆን፣የትምህርት አሰጣጡም በተለያዩ መርጃ መሳሪያዎች የታገዘ ነው፡፡ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተማሪዎችም በዚሁ ትምህርት ቤት ትምርታቸውን ለመከታተልያቀናሉ፡፡ከማየት ችግር በተጨማሪ ሌላየአካል ጉዳትያለባቸው ተማሪዎችም በልዩ ትምህርት ክፍል ውስጥ ይስተናገዳሉ።












