Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

የሆሊውዱ ኮከብ አርኖልድ ሸዋዚንገር

May 23, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ግንቦት 15 2016| NBC ETHIOPIA- የተወለደው በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ሐምሌ 30 ፣ 1947 በደቡባዊ ኦስትሪያ በግራዝ ከተማ አቅራቢያ ታል በተባለች መንደር ሲሆን፣ ገና በለጋ እድሜው ፣የሰውነት ግንባታ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ፊልሞች መመልከት፣ እግር ኳስ፣ ቦክስ እና ዋናን ጨምሮ በስፖርት ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንደነበረው ይነገርለታል።

የሆሊውድ መንደር ኮከቡ ኦስትሪያዊ እና አሜሪካዊ ተዋናይ፣ ነጋዴ፣ የቀድሞ ፖለቲከኛ እንዲሁም ፕሮፌሽናል ቦዲ ቢውልደር፣ አርኖልድ አሎይስ ሸዋርዜንገር።

ታዋቂው የሆሊውድ ተዋናይ ሸዋርዜንገር ክብደት ማንሳት ጀመረው ገና የ15 አመት ልጅ ሳለ ነበር ።

ከልጅነቱ ጀምሮ ቦዲ ቢውልደር መሆን ህልሙ እንደነበር የሚናገረው፣ ሸዋርዜንገር በአውሮፓ በበርካታ ውድድሮች ላይ በአካላዊ ብቃት እና በሰውነት ግንባታ ለመወዳደር ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው።

እ.ኤ.አ በ1968 በ21 አመቱ ወደ አሜሪካ በማቅናት የህይወቱን የሰኬት መንገድ ይጀምራል።በዚያኑም ዓመት ሸዋርዜንገር ሚስተር ዩኒቨርስን በመቀጠልም ሚስተር ኦሎምፒያ ለተከታታይ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ ህልሙን እውን ማደረግ ቻለ ።

በሀገረ አሜሪካ ዝናን ለመቆናጠጥ ጊዜ ያልፈጀበት ሸዋርዜንገር በአስደናቂው የሰውነት ገጽታው ትኩረትን በመሳብ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪ ጎራ እንዲል ጥያቄዎች ይቀርቡለት ጀመረ።

እ.ኤ.አ በ1970 የመጀመሪያውን ሄርኩለስ የተሰኘውን እና በአርተር አላን ሴይድልማን ዳይሬክት የተደረገውን የአሜሪካ አስቂኝ ፊልም ላይ በትወና መሳተፍ ቻለ። ይህም ለዛሬው የሸዋርዜንገር የትወና ስኬት በር የከፈተ ነበር፡፡

በመቀጠልም እ.ኤ.አ በ1977 በሰውነት ግንባታ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው ‹‹ፓምፒንግ አይረን›› በተሰኘው  ዘጋቢ ፊልም ላይ በትወና ተሳተፈ። ከአመታት በኋላ በ1982  ኮናን ዘ ባርባሪያን በተሰኘ ልብ አንጠልጣይ እና በወቅቱ ተወዳጅነትን ባተረፈ ፊልም ላይ በመሪ ተዋናኝነት ተጫወተ፡፡ ፊልሙ በአካዳሚ ኦፍ ሳይንስ፣ ፊክሽን፣ ፋንተሲ ኤንድ ሆረር ፊልም ተሸላሚ መሆን የቻለ እና ለሸዋርዜንገር ሽልማት እና ዝናን ያስገኘለት ነበር፡፡

ከሁለት ዓመት በኋላም የሳይንሳዊ ልብ ወለድ ዘውግ ባለው በጄምስ ካሜሮን ዳይሬክት የተደረገው ፣  የአሜሪካ ሳይንሳዊ ልብወለድ The Terminator1 እና Terminator 2 በተሰኙ ፊልሞች ብቃቱን አስመሰከረ፡፡  ፉልሙም ሮቦቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ አለምን እንደሚቆጣጠሩ ያስመለክታል።

ሸዋርዜንገርም የጎልደን ግሎብ ሽልማት፣የኒኬሎዶን Kids’ Choice Awards፣ የኤምቲቪ ፊልም ሽልማትን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ ሽልማቶች በድንቅ ብቃቱ ማሸነፍ ችሏል።በ Best Male Performance በTerminator 2: እና Judgment Day የኤም ቲቪ አዋርድ አሸናፊ ሆኗል።

ከዚያም Judgment Day ፣ Commando፤ The Running Man , Predator, Total Recall እና , የተሰኙ ፊልሞችን ጨምሮ ከ40 በላይ ተወዳጅነት ባተረፉ ፊልሞች ላይ በትወና ተሳትፏል።

የዘርፈ ብዙ ሞያዎች ባለቤት ፣ ሸዋርዜንገር እ.ኤ.አ ከ1990 እስከ 1993፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እና የስፖርት ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆንም አገልግሏል። በኋላም በካሊፎርኒያ የአካል ብቃት እና ስፖርት ምክር ቤት በገዥው ፒት ዊልሰን ስር ሆኖ አገልግሏል። በስፖርቱ ዘርፍ ስሙ በጉልህ የሚነሳው ሸዋርዜንገር የባህል፣ የትምህርት እና የማህበረሰብ ማበልፀጊያ ፕሮግራሞችን ለወጣቶች የሚያቀርብ ICG የተባለ ፋውንዴሽንን መመስረት ችሏል፡፡ ፋውንዴሽኑ በሀገሪቱ በ15 ከተሞች የሚሰራ ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ250ሺ በላይ ህጻናትን እና ከ400 በላይ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ያገለግላል።

ሸዋርዜንገር በሰውነት ግንባታ በዓለም ታዋቂ ሆኖ ቆይቷል፤ በስፖርቱ ላይ በርካታ የሚባሉ  መጽሃፎችን አበርክቷል፡፡ የምንጊዜም ታላቅ ቦዲ ቢውልደር በሚል ስሙን በጉልህ አኑሯል፡፡ በስፖርቱ ዓለም ትልቅ አበርክቶ ካሳረፉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አንዱም ሲሆን፣ ይህም የክብር አምባሳደርነትን እስከማግኘት አድርሶታል፡፡

ሸዋርዜንገር በፖለቲካ ተሳትፎውም የሚታወቅ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከ2003 እስከ 2011 በካሊፎርኒያ በአስተዳደርነት አገልግሏል። የታይም መጸሄት እ.ኤ.አ ከ2004 እስከ  2007፤ 100 የአለም ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች ብሎ ካስቀመጠው ዝርዝር ሸዋርዜንገር አንዱ ነበር።  ኑሮውን በካሊፎርኒያ ያደረገው የ75 አመቱ አርኖልድ ሸዋርዜንገር፣ አሁን ላይ እርጅና መጣው መጣው ቢለውም እጅ አልሰጥም በማለት የኔትፍሊክስ ቺፍ ኦፊሰር በመሆን ታታሪነቱን እያስመሰከረ ነው፡፡

በ- ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል አለመታወጁ ምርታማነቱ ላይ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ተገለፀ

Next Post

የኬንያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ጉብኝት

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
የኬንያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ጉብኝት

የኬንያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ጉብኝት

ንብረትነቱ የሲንጋፖር አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 777 300ER አየር ላይ የመናወጥ አደጋ አጋጠመው

ንብረትነቱ የሲንጋፖር አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 777 300ER አየር ላይ የመናወጥ አደጋ አጋጠመው

3ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሊካሄድ ነው

3ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሊካሄድ ነው

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?