፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 15 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ አሰሪዎች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አስመልክቶ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ያልወጣ ሲሆን ይህም ምርታማነት ላይ እክል መፍጠሩ ነው በመድረኩ ላይ የተነገረው።

ጉዳዩን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ውይይቶች ሲካሄዱ ቢቆይም እስካሁን ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን የኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አያሌው አህመድ ተናግረዋል።
ከችግሩ ስፋት አንፃር አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል። ጣቢያችን ኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አስመልክቶ ተከታታይ ዘገባዎችን ሲያደርስ መቆየቱ ይታወሳል።
በ-አክረም ኑርያ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












