፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 13 2016| NBC ETHIOPIA-አለም አቀፍ ተቀባይነትን ባተረፉ ፊልም ጸሀፊያን የሚጻፉ እና ታዋቂ ተዋንያኖች የሚሳተፉባቸው ፊልሞች ተቀባይነታቸው ከፍ ያለ እና በጉጉት የሚጠበቁ ናቸው ፡፡
ለፊልም አፍቃሪያን በያዝነው የፈረንጆቹ ግንቦት ወር ለእይታ ይበቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ የባህር ማዶ ፊልሞችን የመራረጥናቸውን ልናደርሳቹ ወደድን፡፡ በሳይንስ ልቦለድ ጽሁፎቹ በሚታወቀዉ Josh Friedman ተጽፎ በ Wes Ball ዳይሬክት የተደረገው Kingdom of the Planet of the Apes የተሰኘው ፊልም በያዝነው ወር ለእይታ ይበቃሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው ፡፡

ፊልሙ ከዚህ ቀደም ሶስት ክፍሎች ሲኖሩት በፊልም ተመልካቾች ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነትን ማትረፍ ችሏል፡፡
የሳይንስ ልቦለድ እና አክሽን ዘውግ ያለው ፊልሙ ከበፊቶቹ ክፍሎች የቀጠለ ሲሆን አንድ ዝንጀሮ የራሱን ግዛት ገንብቶ የሚያደርገውን ጦርነት የሚያሳይ ነው፡፡ ከ160 እስከ 165 ዶላር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡ በJohn Krasinski ተጽፎ ዳይሬክት የተደረገው IF የተሰኘው አስቂኝ የቤተሰብ ፊልም ዘውግ ያለው ፊልም ሜይ 17 ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፊልሙም የሚያጠነጥነው በህይወቷ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የገባች ቤያ የተባለች ወጣት ልጅ ሳታስበው ምናባዊ ወይም IF የተባሉ ጓደኞች የማየት ችሎታ ታገኛለች፡፡ በዚህም ካል ከተባለ ከሱዋ ጋር ተመሳሳይ ችሎታ ካለው ልጅ ጋር በመሆን እነዚህን ለሁለቱ ብቻ የሚታዩትን ምናባዊ ፍጡሮችን ወደ ነበሩብት ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት በሳቅ እያዋዛ የሚያቀርብ ፊልም ነው፡፡
ሮቦት ደሪም በዚህ ወር ከሚጠበቁ ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው ፡፡

በ1980 በኒውዮርክ ከተማ ብቻውን ይኖር የነበረ አንድ ውሻ በቴሌቭዝን ማስታወቂያን ተመልክቶ ሮቦት የተባለች ሮቦትን ገዝቶ ጓደኛ ሲሆኑ እና በኃላ ላይም በአንድ ዉሃ ዳርቻ ላይ ከተጠፋፉ በኃላ ውሻው ሮቦቱን ለማገኘት የሚያደርገውን ጥረት የሚያሳይ ፊልም ነው ፡፡ በፊልሙ ላይ ያሉ ንግግሮችም ቀልዱችን እና ብልሃተኛ ሀሳቦች ያካተቱ መሆናቸው ተገልጾል፡፡ ፊልሙም 1 ሰአት ከ 42 ደቂቃ ርዝመት አለው፡፡ በፈረንጆቹ ሜይ ዘጠኝ በጀርመን እና ሜይ 31 በ አሜሪካ ለእይታ በቅቷል፡፡
በአንድ ወቅት ላይ የእንግሊዝ ታዋቂ ዘፋኛ ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ በነበረቸው እና እ.ኤ.አ በ2011 ህይወቱዋ ያለፈው Amy Winehouseን የህይወት ታሪክ መሰረት አድርጎ የተሰራው Back to Black የተሰኘ ፊልም በአሜሪካ እና ካናዳ በ ሜይ 17 ለእይታ በቅቷል፡፡

ፊልሙም በMatt Greenhalgh ተጽፎ በ Sam Taylor-Johnson ዳይሬክት ተደርጓል፡፡ Amy Winehouse በመሆንም Marisa Abela ዋና ገጸባህሪዋን ተጫውታዋለች፡፡
The Beach Boys በፖፕ ሙዚቃ አንጋፋ የሆነው እና በብሪያን ፣ ካርል እና ዴኒስ ዊልሰን የተባሉ ወንድማማቾች በ1961 የተመሰረተውን ታዋቂዉን የሙዚቃ ባንድ ዙሪያ የተሰራው አዲስ ዘጋቢ ፊልሌላኛው ተጠባቂ ፊልም ነው፡፡ ዘጋቢ ፊልሙም ሜይ 24 በ ዲዝኒ ፕላስ ይለቃቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ም













