፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 13 2016| NBC ETHIOPIA-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “አካል ጉዳተኞች መስራት ይችላሉ “በሚል መሪ ሀሳብ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፍቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይንሸት ዘሪሁን አካል ጉዳተኞች መስራት አይችሉም የሚለውን የተዛባ አመለካከት በመለወጥ፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ ምርታማ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት እንዲሁም በእውቀት እና በክህሎት በልፅገው የራሳቸውን ገቢ ማግኘት እንዲችሉ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በአንዳንድ ክፍለ ከተማዎች ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሲከናወን የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አምራች አካል ጉዳተኞችን በአንድ ምርቶቻቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ መደረጉ ተገልጿል።
ለተከታታይ አምስት ቀናት ቆይታ በሚኖረው ባዛሩ ማህበረሰቡ የአካል ጉዳተኞቹን ለማበረታት ምርቶቻቸውን እንዲሸምቱ ጥሪ ቀርቧል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












