፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 09 2016| NBC ETHIOPIA-የዓለም የከፍተኛ ደም ግፊት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሃያኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።
ጤና ሚኒስቴር “የደም ግፊትዎን በትክክል ይለኩ፤ ይቆጣጠሩ እና ረጅም ጤናማ ህይወት ይኑሩ!” በሚል መሪ ቃል ከኢትዮጵያ የኩላሊት ሕመም ማህበር፣ የኢትዮጵያ የልብ ማህበርና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የዓለም የከፍተኛ ደም ግፊት ቀንን እያከበረ ይገኛል።

የደም ግፊት መመርመሪያ መሳሪያዎች እጥረት መኖሩን የገለፀው ሚኒስቴሩ ችግሩን ለመቅረፍ ብሎም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
ቀኑ ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከበር ስለመሆኑ አስታውቋል። ቀኑን ምክንያት በማድረግ የእግር ጉዞ፣ የጤና ምርመራና ሌሎች ፕሮግራሞች ተካሂደዋል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv


See insights and ads
Like
Comment
Share












