፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 09 2016| NBC ETHIOPIA- ዩክሬን ሩሲያ በተቆጣጠረችው ቤልቤክ የአየር ማዘዣ ጥቃት በመፈጸም ሶስት የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ አደርጊያለሁ አለች ።
ኬይቭ ጥቃት አደረስኩ ብትልም የሩሲያ ሀይሎች የዩክሬን ሁለተኛውን ትልቅ ከተማ ካርኪቭን መያዛቸውን ተናግረዋል።
የሩሲያ ግስጋሴ ስጋት የፈጠረባው ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ወታደሮቻቸው የአይበገሬነት ስሜት እንዲያድርባቸው አነቃቅተዋል ነው የተባለው ፡፡
ዘለንስኪ ካርኪቭን ለሞስኮ አሳልፎ መስጠት የማይታሰብ ነው ያሉ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲያደረግላቸው አሳስበው ይህ ካልሆነ ለዩክሬን መሸነፍ ተጠያቂው መላው ዓለም ነው ብለዋል ።
ሮይተርስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












