፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 09 2016| NBC ETHIOPIA- ፊሊፒንስ በደቡብ ቻይና ባህር ላይ የምታደርገውን ትንኮሳ እንድታቆም ቻይና አሳሰበች።
የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ፊሊፒንስ በግዴለሽነት እርምጃ ከመውሰድ እንድትቆጠብ እና በደቡብ ቻይና ባህር ላይ የሚደርሰውን ትንኮሳ እንድታቆም አስጠንቅቋል።
የቤጅንግ ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው የቻይና ጦር ችግር መፍጠር አይፈልግም፣ ችግር ከመጣ ግን አንሸሽም ፤ በተጨማሪም የግዛት ሉዓላዊነት፤ የባህር መብቶች እና ፍላጎቶችን በደቡብ ቻይና ባህር በማስጠበቅ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር እናደርጋለን ማለታቸውን ሲ ጅቲ ኤን ዘግቧል ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












