Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

በመድኃኒት ምክንያት የሚከሰት የጉበት ጉዳት/DRUG INDUCED LIVER INJURY-DILI/

May 15, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

አዲስ አበባ | ግንቦት 07 2016| NBC ETHIOPIA- ጉበት ትልቁ የሰውነት ክፍል ሲሆን ከ1-1.5 ኪግ ይመዝናል። ጉበት በጅማቶችና አያያዥ ሕዋሳት አማካይነት በጨጓራ፣ አንጀት፣ ድልሺ፣ እና ትላልቅ ደም ሥሮች ተከቦ በቀኝ የላይኛው ሆድ ክፍል ውስጥ ከታችኞቹ የጎድን አጥንቶቻችን ሥር ይገኛል።

1/4ኛው ከልብ የሚረጨው ደም ለጉበት ይላካል። ጉበት በሰውነታችን ውስጥ የሚከናወኑ ተግባሮችን ሚዛን(Homeostasis) በመጠበቅ ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው። ይህም እጅግ አስፈላጊ ፕሮቲኖች(አልቡሚን፣ ሆርሞንና ኢንዛይም ተሸካሚ ንጥረነገሮች፣ ለደም እርጋታ ለእድገት እና ለዑደተሕይወት የሚጠቅሙ)፣ ሃሞት ያመርታል፣ የሰውነት የስኳር እና የስብ መጠን ይቆጣጠራል።

የጉበት በሽታ ሥርጭት

የጉበት በሽታ በ2020 በዓለም ዙሪያ ወደ 1.5 ቢሊዮን የሚጠጉ ግለሰቦችን የጎዳ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ችግር ነው።የጉበት በሽታ የተለያዩ መንስኤዎች ሲኖሩት ሥር የሰደደ  አልኮል ተጠቃሚነት፣ የቫይረስ ሄፓታይተስ ቢ፣ ሲ እና ዲ ኢንፌክሽኖች፣ አልኮል ያልሆነ የስብ ጉበት በሽታ (NAFLD)፣ የጉበት ብግነት እና ድኅረ መድኃኒት የጉበት ጉዳት ዋነኛ መንስኤዎች ሲሆኑ በሃገራችን ደግሞ የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ ዋና ዋና መንስኤዎች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

በዚህ ጽሑፍ ያለ መጠን በተወሰደ መድኃኒት ምክንያት ስለሚከሰት የጉበት መጎዳት ምን እንደሆነ እንናስረዳችኃለን፡፡

ድኅረ-መድኃኒት ጉበት ጉዳት/ ዲሊ(DILI) ምንድነው?

ለተለያዩ በሽታዎች በሐኪም ማዘዣ ሊሆን ይችላል ያለ ማዘዣ የወሰድናቸው መድኃኒቶች እንዲሁም ከእጽዋት የተቀመሙ የባህል መድኃኒቶች ጉበት ላይ ጉዳት ሲያስከትሉ የሚገጥመን የጤና ዕክል ነው። ከዕፅዋት የተቀመሙ መድኃኒቶችን እንደ መድኃኒትነት መጠቀሙ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት የመጣ ሲሆን ከብዙ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በታሪክ ማስረጃዎች ተመዝግቧል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በምዕራባውያን ማህበረሰቦች ውስጥ ከዕፅዋት የተቀመሙ መድኃኒቶች  አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በተለይም ለሰውነት ግንባታ ፣ ክብደት ለመቀነስ እና “ጥሩ ጤና”ን ለመጠበቅ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው። ይህም በሕዝቡ ውስጥ በሰረጸው ምርቶቹ ተፈጥሯዊ ስለሆኑ ምንም ጉዳት የላቸውም በሚል  የተሳሳተ  እምነት ስለተደገፈ ነው። በተቃራኒው ግን ከዕፅዋት የተቀመሙ ምርቶች ከፍተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶችን እንደፈጠሩ ጥናቶች ያሳያሉ።  ከእነዚህም መካከል ንቅለተከላ የሚያስፈልገው ወይም ለሞት የሚዳርግ አጣዳፊ የጉበት ጉዳት በዋናነት ተደጋግሞ ተገልጿል::

የዲሊ መንስኤዎች

ከዕፅዋት የተቀመሙ መድኃኒቶች ጋር የተዛመደ የጉበት ብግነት በምዕራባውያን አገሮች ውስጥ ሁለተኛው በጣም የተለመደው ድኅረ-መድኃኒት የጉበት ጉዳት (DILI) ሲያስከትሉ በምስራቁ  ክፍል ውስጥ ደግሞ ዋነኛ የዲሊ መንስኤ ናቸው። ለቲቢ፣ ኢችአይቪ/ኤድስ፣ ካንሰር፣ ለአእምሮ  እና ለሌሎችም ሕመሞች የሚታዘዙ መድኃኒቶች በዋናነት ሲጠቀሱ ያለማዘዣ የሚወሰዱ የሕመም ማስታገሻዎችም ፓራስታሞልን ጨምሮ ተጠቃሽ ናቸው።

የዲሊ ምልክቶች

-የዓይን ቢጫ መሆን/መደፍረስ፣ ትንሽ እንደተንቀሳቀሱ የድካም ስሜትና መዛል፣ ማሳከክ፣ የቀኝ ላዕላይ ሆድ ክፍል ህመም፣ ደም ማስመለስ፣ ከሆድ የሚጀምር የሰውነት ዕብጠት፣ የሰገራ እና የሽንት ቀለም መቀየር፣

ዲሊ ሊያስከትል የሚችለው ውስብስብ የጤና እክል ምንድን ነው

-ድንገተኛና አደገኛ የጉበት መድከም(Fulminant hepatic failure)

-ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ(Chronic liver disease)

-የመጨረሻ ደረጃ የጉበት መኮማተር(Cirrhosis)

ሕክምናው

Liver treatment. Doctors study the internal organs of the liver and gallbladder, hepatic duct. Structure internal organ. Vector illustration flat design. Isolated on white background.

ሕመምተኛው የወሰደውን መድኃኒት ወይም የተጠቀመውን ዕጽ የመርዛማነት ክብደት ቀድሞ ማወቅ ሊያስከትል የሚችለውን የጤና ዕክል ደረጃ ለመተንበይ እና አጣዳፊ የጉበት ድካምን ለመከታተል ይረዳል። በመድኃኒት/በዕጽ ምክንያት ለሚመጣው የጉበት ጉዳት ዋናው የሕክምና ዘዴ መድኃኒቱን/ዕጹን ከመጠቀም ማቋረጥ ነው።

አስከፊ ጉዳት ካስከተለ ግን  ድጋፍ ሰጪ ሕክምና ያስፈልጋል። ከዛም ከባሰ የጉበት ንቅለ ተከላ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል።

መከላከያ መንገዱ

-ጉበትን ሊጎዱ የሚችሉ አልኮል እና ሌሎች መድሃኒቶችን ማስወገድ

-የመጨረሻ ደረጃ የጉበት መኮማተር(Cirrhosis) በሽታ ያለባቸው ሰዎች ጉበትን እንደሚጎዱ ከሚታወቁ ነገሮች ሁሉ መራቅ አለባቸው። ለምሳሌ፡-

-ከአልኮል

-ስቴሮይድ ካልሆኑ ፀረ-ብግነት መድኃኒቶች(NSAIDs) ለምሳሌ ጎፈን(ibuprofen, naproxen)

እንደ ካቫ ያሉ አንዳንድ ማሟያዎች እና ከዕፅዋት የተቀመሙ መድኃኒቶች

ትኩሳት ፣ ህመም እና ሌሎች የተለመዱ በሽታዎችን ለማከም ብዙ የሚገዙ እና በሐኪም የታዘዙ መድሃኒቶች አሲታሚኖፌን ይይዛሉ። ስለሆነም ፓራሴታሞል/ፓናዶል (acetaminophen)  በቀን ከ2 ግራም በላይ መውሰድ የለባቸውም።

ጉበትን ለመከላከል የሚወሰዱ ክትባቶች—— የሄፐታይተስ ኤ እና ቢ መከላከያ የሆኑ ክትባቶች በጉበት ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ይረዳሉ። ኢንፌክሽኖች በተለይ በሲሮሲስ በተያዙ ሰዎች ላይ ከባድ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ከጉንፋን የሚከላከሉ ክትባቶችን (በዓመት አንድ ጊዜ)፣ የሳንባ ምች (ቢያንስ አንድ ጊዜ)፣ ዲፍቴሪያ እና ቴታነስ (በ10 ዓመት አንዴ) እና ሌሎች ክትባቶችን መውሰድ አስፈላጊ ነው።

Tags: drug induced liver injuryliverliver health
ShareTweetShare
Previous Post

ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ቀን እየተከበረ ነው

Next Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

በህንድ የተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት መጠን

በህንድ የተከሰተው ከፍተኛ የሙቀት መጠን

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?