፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 05 2016| NBC ETHIOPIA- በዳርፉር ቁልፍ ከተማ በሆነችው አል-ፋሸር ውስጥ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱንና 27 ንጹሀን ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቀ፡፡
ከዓርብ ጀምሮ በከተማዋ ላይ በአየር ድብደባ፣ በመድፍ እና መትረየስ የታገዘ ጦርነት እንደነበር ተገልጿል ፡፡

በጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሀን እና ተቀናቃኛቸው ሙሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ሀይሎች መካከል እስካሁን በተደረገው ጦርነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን መፈናቀላቸውን ያስነበበው ቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












