፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 02 2016| NBC ETHIOPIA-የእስራኤልን የዩሮቪዥን የዘፈን ውድድር ተሳትፎ በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በስዊድን የወደብ ከተማ ማልሞ ሰልፍ መውጣታቸው ተገለጸ፡፡

ዝግጅቱ ከፖለቲካ ውጪ መሆን አለበት የሚሉት የውድድሩ አስተባባሪዎች እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጦርነት ምክንያት እንድትገለል የቀረበላቸውን ጥሪ ተቃውመዋል ተብሏል ።
እንደ አልጀዚራ ዘጋባ የዩሮቪዥን የሙዚቃ ኮንሰርት አውሮፓውያን ስመ ጥር ዘፈኞቻቸውን በመላክ ሚወዳደሩበት ነው፡፡ የዘንድሮው ዩሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር በስዊድን ይካሄዳል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












