የደም ግፊት ምንድን ነው ?

ደም በደም ወሳጅ ቧንቧዎች(Arteries) ላይ የሚያሳድረው ግፊት ነው።
የደም ግፊት እንዴት ይገለጻል ?

???? ሲስቶሊክ የደም ግፊት፦ልብ ደም ለመግፋት በሚኮማተርበት ግዜ የሚኖረው የግፊት መጠን ነው።
???? ዲያስቶሊክ የደም ግፊት፦ልብ ዘና(relax) በሚልበት ግዜ የሚፈጠር የግፊት መጠን ነው

ከፍተኛ የደም ግፊት የምንለው መቼ ነው ?
???? የደም ግፊታችን 140/90 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው።
???? ጤነኛ የደም ግፊት የምንለው የደም ግፊታችን 120/80 በታች
???? 120-139/80-89 ሲሆን ደግሞ ቅድመ-ከፍተኛ የደም ግፊት (Pre-hypertension) እንለዋለን
የከፍተኛ የደም ግፊት መንስዔዎች

???? መንስኤውን መሰረት በማድረግ ከፍተኛ የደም ግፊት በሁለት ይከፈላል፦
1. መንስኤው የማይታወቅ ከፍተኛ የደም ግፊት(Essential /primary hypertension)
ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ መንስዔ የሌላቸው ሲሆኑ ምንአልባትም በአካባቢያዊና በዘር ውርስ ምክንያቶች(Environmental and genetic factors) ይመጣሉ ተብሎ ይታመናል። ከ80-95% ይይዛሉ
2. መንስኤው የሚታወቅ ከፍተኛ የደም ግፊት(Secondary hypertension)
ይህ የደም ግፊት ሊታወቅ የሚችል ብሎም የሚታከም መንስዔ ያለው
ምሳሌ ፦በኩላሊት ህመም አማካኝነት ሊመጣ የሚችል ከፍተኛ የደም ግፊት ተጠቃሽ ነው።ከ5-20% የሚሆነውን ይይዛሉ
ለደም ግፊት የሚያጋልጡ ምክንያቶች
???? የእድሜ መግፋት ፦በተለይም እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶችና ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል።
???? ዘር፦-ከፍተኛ የደም ግፊት ብዙን ግዜ ከነጮች በበለጠ በጥቁሮች(Blacks) ላይ የሚስተዋል ሲሆን የሚያስከትለው ጉዳትም ከፍ ያለ ነው።
???? በበሽታው የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ መኖር
???? ከመጠን ያለፈ ውፍረትና የሰውነት ክብደት
???? የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ
???? ሲጋራ ማጨስ
???? የአልኮል መጠጦችን ማዘውተር
???? ከመጠን ያለፈ ጭንቀት
???? ጨው የበዛባቸውን ምግቦች መመገብ
የበሽታው ምልክቶች

???? የከፍተኛ ግፊት በሽታ አብዛኛውን ግዜ ምልክት አያሳይም ስለዚህ ያለን ብቸኛው አማራጭ የክትትል ምርመራ ማድረግ ነው። ነገር ግን ግፊታችን ከመጠን በላይ ሲጨምር የሚከተሉትን ምልክቶች ልናይ እንችላለን
???? ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት
???? የእይታ ችግር
???? የድካም ስሜት
???? የደረት ህመም
???? ለመተንፈስ መቸገር
???? የልብ ምት መዛባት
???? ልባችን ሲመታ ለራሳችን መታወቅ
???? ራስን መሳት ወይም የሰውነት መንዘፍዘፍ
???? የሰውነት መስነፍ ወይም መደንዘዝ
???? ለማወራት መቸገር
???? ማስታወክና ማቅለሽለሽ
???? ደም የቀላቀለ ሽንት
መቼ የህክምና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል?
???????? ከላይ በዝርዝር የጠቀስናቸውን ምልክቶች ካስተዋሉ የህክምና ባለሙያ ማናገር ያስፈልጋል በተለይ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለቦት ካወቁ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።












