፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 02 2016| NBC ETHIOPIA- በርካታ የፋሽን ትርዒቶች አያጧትም፣ አለም አቀፍ ይዘታቸው ደግሞ ከየአህጉሩ የታዳሚዎችን ቀልብ እንዲሳቡ ያደርጋቸዋል በሀገረ አሜሪካ በየአመቱ የሚካሄዱ ሁነቶችን….የፈረንጆቹ ግንቦት በገባ በመጀመሪያው ሰኞ የሚካሄደው ሜት ጋል የተሰኘው ተወዳጅ የፋሽን ዝግጅት ዓመቱን ጠብቆ ዘንድሮም ተካሂዶል፡፡
ሜት ጋል አለም አቀፍ እውቅናን ያተረፉ እና ተጽኖ ፈጣሪ ሰዎች በሚገኙበት የሚካሄድ ደማቅ ዓመታዊ የፋሽን ምሽት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ1948 አዲስ ለተቋቋመ ተቋም የገንዘብ ማሰባሰብያ ታስቦ ጅማሮውን ማድረጉን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ የፋሽን ሁነት በኒውዮርክ ለሚገኘው ለሜትሮፖሊታን የአርት ሙዚየም እና አልባሳት ተቋም ገቢ ማሰባሰቢያ ሆኖ በየአመቱ ይዘጋጃል፡፡

ታዋቂ ተዋንያን፣ ዘፋኞች፣ ሞዴሎች እና ዲዛይነሮች በየአመቱ በዚህ የፋሽን ምሽት ላይ በተለየ ጥበብ የተሰሩ ልብሶችን በመልበስም ይታደማሉ፡፡ ይህንንም ዝግጀት በአለም ዙሪያ ያሉ በርካታ የፋሽን አድናቂዎች በጉጉት ይጠብቁታል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ቢሆኑ ቀድመው ስለ ዝግጅቱ መረጃዎችን ማሰራጨት ይጀምራሉ፡፡
የልበስ ዲዛየነሮች በየአመቱ አዘጋጆቹ በሚያወጡቱት የልብስ ጭብጥ መሰረት የተለያዩ ይዘት ያላቸውን እና ያልተለመዱ ንድፎችን ሰርተው ታዋቂ ሰውችን በማልበስ ችሎታቸውን የሚያሳዩብትም መድረክ ነው፡፡
በጊዜ ሂደት አዳዲስ ነገሮችን እያካተተ እዚ የደረሰው ሜት ጋል በጅማሮው ወቅት የመግቢያ ትኬት በ50 ዶላር እንደተሸጠ ይነገራል፡፡ ባሳለፍነው አመት በነበረው ዘግጅት ላይ የመግቢያ ትኬት 50 ሺ የተሸጠ ቢሆንም በዚኛው አመት ግን 75ሺ ዶላር መሸጡ ተሰምቷል ፡፡
ዝግጅቱን መታደም የበርካቶች ህልም ቢሆንም መግቢያ ትኬቱን የሚግዙት በአዘጋጆቹ የተመረጡት ታዋቂ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ እነዚ የተመረጡ ሰዎችም የዝግጅቱ ዋና እና ተጠባቂ የሆነው የቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርአት ላይ እስኪታዩ በሚስጥር የሚያዝ ይሆናል፡፡ ይህም ዝግጅቱን በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት ያደርገዋል፡፡
በኒውዮርክ ከሚገኙ የገቢ ማሳባሰቢያ መርሃግብሮች ግንባር ቀደም መሆን የቻለው ዝግጅቱ ባሳለፍነው አመትም 22 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳስገባ ይነገራል፡፡


በዘንድሮ አመት በተካሄደው ዝግጅት ላይም The Garden of Time በሚል ጭብጥ ዲዛይነሮች በነደፉት ልብስ ታዋቂ ሰዎች ደምቀውበት አልፏል፡፡
ሃሳቡም ያረጁ እና የቆዩ ልብሶችን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዴት እንደ አዲስ ህይወት እንደሚዘራባቸው ለማሳየት ያቀደ ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይም እንደ ብርቅ ከታዩ እና የሰውን ቀልብ የሳቡ ከተባሉት አለባበሶች መካከል አቀንቃኟ ካሚላ ካቤሎ የያዘቸው የበረዶ ቦርሳ እና 250ሺ ክሪስታሎችን የያዘው፣ ለመስራትም 450 ሰአትን የፈጀው ልብስ ይጠቀሳሉ፡፡
ሌላኛዋ ሜት ጋል ድምቀት የሆነቸው ጂጂ ሀዲድ የለበሰችው ቀሚስ ሲሆን፣ ቀሚሱን ለመስራት ከ70 ሰዎች በላይ እንደተሳተፉና ከ13,500 ሰአታት በላይ እንደፈጀም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዝግጅቱንም በ Vogue ድረገጹ ላይ በቀጥታ ስርጨት በሚሊዮን የመሚቆጠሩ ሰዎች ተመልክተውታል፡፡
በ-የአብስራ ብርሃኑ












