፨ ፨ ፨ ፨ ፨አዲስ አበባ | ሚያዚያ 29 2016| NBC ETHIOPIA-ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጤታማነት የግል ኩባንያው ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተመላከተ፡፡
-የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል፡፡
-በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ከክረምት በፊት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ።
-የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ያለምንም እክል ማረፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቹን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረድ ችለዋል።
-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልማትን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።
-በሀገር አቀፍ ደረጃ መካሄድ የጀመረውን የ“ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄ ጤና ሚኒስቴር “የጽዱ ኢትዮጵያ ጽዱ ጤና ተቋማት ለተሟላ ጤንነት!” በሚል መሪ መልዕክት ጤና ተቋማትን ንጹ በማድረግ ህብረሰተብን ጤናማ የማድረግ አላማን አንግቦ ንቅናቄውን መቀላቀሉን ሚንስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገልፀዋል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












