፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 26 2016| NBC ETHIOPIA- የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለእስራኤል የሚያደርገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ የአሜሪካን የውስጥ ህግ የሚሰጥስ እና በጦርነት ትርፍ የሚፈልግ ነው ሲሉ የቀድሞዋ የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ሀላ ራሪት ተናገሩ፡፡
ዋሽንግተን የምታደርገው ያልተገባ የጦር መሳሪያ ልገሳ ራስን ለመከላከል ያለመ ሳይሆን ወደ ማጥቃት ያዘነበለ መሆኑን ነው ሀላ ተናገሩት፡፡ የባይደን አስተዳደር በመካከለኛው ምስራቅ የሚከተለው ፖሊሲ ወድቋል በማለት አጥብቀው በመተቸት የሚታወቁት ሀላ ራሪት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች ሲሉ በመሞገትም ይታወቃሉ፡፡
የቀድሞዋ የስቴት ዲፓርትመን ቃል አቀባይ ሀላ በቅርቡ በፍቃዳቸው ስራቸውን የለቀቁ መሆናቸውን ያስነበበው ቲ አር ቲ ወርልድ ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












