Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የቆዳ አስም (የቆዳ አለርጂ) ምንድን ነው?

May 6, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የጤና እክሎች

የቆዳ አስም (የቆዳ አለርጂ) የተለመደ የቆዳ በሽታ ዓይነት ሲሆን፤ ቆዳን በማድረቅ እና በማሳከክ የቆዳን ብግነት ወይም መጉረብረብ (Inflammation) የሚያመጣ ሕመም ነው።

ይህ በሽታ በአብዛኛው እስከ አምስት ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይ ይከሰታል፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም ሕፃናት እድሜአቸው እየጨመረ ሲሄድ ምልክቶቹ እየጠፉ ይሄዳሉ።

ስለዚህም ብዙውን ጊዜ ይህ በሽታ አለርጂ፣ አስም ወይም ደግሞ በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ባላቸው ሰዎች ላይ ይከሠታል። ስለዚህም ተመሳሳይ ችግር ከአለባቸው ወላጆች ወይም እናትና አባት የተወለዱ ሕፃናት፤ ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ የቆዳን እርጥበት የሚጠብቁ ቅባቶች ቢጠቀሙ ቢያንስ እስከ አንድ ዓመታቸው ድረስ በቆዳ አስም የመያዝ ዕድላቸው ዝቅተኛ ይሆናል።

የቆዳ አስም ምልክቶች ምንድናቸው?

ሰዎች በቆዳ አስም በሚጠቁበት ጊዜ ቆዳቸው የማሳከክ፣ የመድረቅ፣ የመሻከር፣ ዉሃ የቋጠረ ቀይ ሽፍታ እና የመቆጣት ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። ምልክቶቹም ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፉ ሲሆን፤ እየጠፉ ተመልሰው በመምጣትም ረጅም ጊዜ የመቆየት ጠባይ አላቸው። 

የቆዳ አስም ብዙ ጊዜ እንደ ታማሚዎች የዕድሜ ክልል የተለያየ መልክ ይኖረዋል።

ለምሳሌ፡- ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ በእጃቸው፣ በእግራቸው፣ በጉንጭ ወይም በጭንቅላታችቸው ላይ ይወጣል፡፡ ነገር ግን ዳይፐር (ሽንት ጨርቅ) አካባቢ ያለውን የሰውነት ክፍል ብዙውን ጊዜ አያጠቃም።

በትላልቅ ልጆች እና አዋቂዎች ላይ ብዙውን ጊዜ የአንገት አካባቢ፣ የክርን መሰንጠቂያዎችን እና የጉልበት ጀርባዎች ላይ የሚወጣ ሲሆን፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ በእጅ፣ በእግር፣ በክንድ እና በፊት ላይ ሊወጣ ይችላል።

በትላልቅ ልጆች እና አዋቂዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ  ቆዳው እየጠነከረ ሊሄድ እና ከብዙ ማከክ የተነሣ ጠባሳ ሊፈጥር ይችላል።

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ከአለዎት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ሐኪምዎን ያነጋግሩ።

የቆዳ አስም እንዴት ይታከማል?

ምንም እንኳን ዘላቂ የሆነ ፈውስ ማምጣት ባይቻልም ምልክቶቹን ግን በሕክምና ማስታገስ  ይቻላል። በአንፃሩ በአግባቡ ካልታከመ የማያቋርጥ ማሳከክ እና የቆዳ ጠባሳን ሊያመጣ ይችላል። ይህም ለበሽታ አምጪ ተህዋስያን ሊዳርግ ብሎም የቆዳ ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል።

በአጠቃላይ የቆዳ አለርጂ ሕክምናው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች እና መድኃኒቶችን ያካተተ ይሆናል፡፡

ምን ዓይነት የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ማድረግ አለብኝ?

ቆዳችን እንዳይደርቅ የቆዳን እርጥበት የሚጠብቁ ሽታ አልባ ክሬሞችን እና ቅባቶችን (Moisturizer) መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ እንዲሁም የሚከተሉትን የሐኪም ምክሮች በመተግበር አለርጂው እንዳይባባስ ማድረግ ይቻላል። እነዚህም ፡-         

-ገላን ከመታጠብ በፊት ወይም ከታጠቡ በኋላ ወዲያውኑ የእርጥበት ክሬምን (Moisturizer) ማድረግ፡፡

-ገላን ከታጠቡ በኋላ በለስላሳ ፎጣ በቀስታ ማድረቅ፤ በጭራሽ በፎጣ አለመፈተግ፤ኢንፌክሽን ሊያስከትል ስለሚችል መቧጠጥን ማስወገድ።

-በጣም ሞቃት ወይም ደረቅ አየር በሚሆንበት ጊዜ ረጠብ ወይም ቀዝቀዝ ያለ ፎጣ ማድረግ፡፡

-ጭንቀት ወይም ውጥረትን መቀነስ፡፡

-ሻካራ ሳሙናዎች ወይም የጽዳት ምርቶችን አለመጠቀም።

-መዓዛ  አልባ ማጽጃዎች፣ መዋቢያዎች እና ሌሎች የቆዳ እንክብካቤ ምርቶችን መጠቀም።

-ኬሚካሎችን በሚይዙበት ጊዜ ሁሉ ጓንት እና መከላከያ ልብሶችን መልበስ።

የቆዳ አለርጂ መድኃኒቶች ምን ምንድን ናቸው?

የጤና ባለሙያው የቆዳ ማሳከክ ወይም ኢንፌክሽን ለማከም እንዲሁም ቀይ ሽፍታዎችን ለማስወገድ እንደ አስፈላጊነቱ የሚከተሉትን መድሀኒቶች ሊያዝ ይችላል። 

-እርጥበት ያላቸው ክሬሞች ወይም ቅባቶች

-ማሳከክን የሚቀንሱ፤ አንቲ ሂስታሚን (Antihistamine)

-የቆዳ ኢንፌክሽን ለማከም፤ አንቲባዮቲክስ (Antibiotics)

-ማሳከክን፣ ሽፍታን፣ እብጠት እና የቆዳ መቆጣትን ለመቆጣጠር፤ ስቴሮይድ ክሬሞች እና ቅባቶች (Topical or oral steroids) ሊታዘዙ ይችላሉ።

ShareTweetShare
Previous Post

በእስራኤል የሚገኙ ኃይማኖታዊ ስፍራዎች

Next Post

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

የሩሲያ ጥቃት በዩክሬን

የሩሲያ ጥቃት በዩክሬን

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?